የጉራጌ ብሔረሰብ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት እና አንፀባራቂ የባህል እሴቶች ካሉት ብሔረሰቦች አንዱ ነው።

ባህል ቤቶች የአካባቢያቸውን ወይም የመጡበት ብሔራቸውን ባህልና ወግ ከማስተዋወቅ አንፃር ሰፊ ስራዎችን መስራትና ሌላው የማያውቀውን ማለትም የባህል ውርርስ ከማስፋት አንፃር ብዙ መስራት የሚችሉበት አጋጣሚ ስላለ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው።

በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የሚገኙ ባህል ቤቶችም የአካባቢው ባህል እንዳይጠፋና ለትውልድ ለማስተላለፍ እየሰሩት ያለው ስራ አበረታች ሲሆን በ ከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ባህል ቤቶች የጉራጌ ባህልና እሴት በከፍተኛ ሁኔታ እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

በከተማዋ ካሉ ባህል ቤቶች መካከል ታብስያ፣የገንየ፣ጀፎረንዳ ፣ድማዳ እንዲሁም ዘምዘም የጉራጌ ባህላዊ ክትፎ ቤቶች ተጠቃሽ ሲሆኑ የአካባቢውን ባህል አጉልቶ ከማስተዋወቅ አንፃር እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ የሚደገፍና የሚበረታታ ነው።

እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በወልቂጤ ከተማ በርካታ ሆቴሎች የአካባቢው ባህል እና እሴት ለማስተዋወቅ እየሰሩ ሲሆን ለአብነትም የጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል የጉራጌ ባህልና ስርዓት ለትውልድ እንዲተላለፍና ለሌላው የማስተዋወቅ ስራ በስፋት እየሰራ የሚገኝ ሆቴል መሆኑ ይታወቃል።

የጉራጌ ማህበረሰብ ለዘመናት ድንቅ የተባሉ እና በብዙዎች ዘንድ አግራሞትን የፈጠሩ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት ብቻ ሳይሆን የብዙ አንፀባራቂ የባህል ቤቶች ባለቤት ነው።

የባህል ቤቶች ጥንታዊውን የጉራጌን ባህልና እሴት ከማጉላት የጉራጌ ማህበረሰብ ባህል እና ስርዓት በመከተል የተለያዩ ዝግጅቶችና ክንዋኔዎች በማከናወን የምግብ አቀራረብ፣ባህላዊ አለባበስ ፣ማህበረሰቡ የሚጠቀምበት ቁሳቁስ በመጠቀም እንዲሁም አጠቃላይ ማህበረሰቡን የሚያስተዋዉቁ ነገሮችን በመጠቀም የበኩላቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።

የጉራጌ ማህበረሰብ የኖረበት የማህበረሰቡ ባህልና ስርዓት ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ለሚደረገው ጥረትና መልካም እንቅስቃሴ የበኩላቸውን እየተወጡ ያሉ ሰዎችን በማመስገን ቀጣይ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል ።

ሲል የዘገበው የወልቂጤ  ከተማ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ነው

ባህል የሰው ልጅ ምክንያታዊ ፍጡር እንዲሆን ያስቻሉትና ከሌሎች ፍጡራን ለመለየት ያበቁት በርከት ያሉ ክንውኖችን የያዘ ሰፊ ዘርፍ ሲሆን አንሲል የወልቂጤ  ከተማ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ነውድ ህብረተሰብ ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅባቸው የአኗኗር ዘይቤዎች ፣እምነቶች እና ትውፊቶች የመሳሰሉት የያዘ ሰፊ ፅንሰ ሀሳብን ያካተተ ነው ።

Previous በግብርናው ዘርፍ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

1 Comment

  • lidiya kamil
    February 12, 2024

    Good

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo