2. የዩኒቱ ራዕይ፣ተልዕኮና እሴቶች

2.1 ራዕይ
በ2022 ዓ.ም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በከተማው ተገንብቶ ለኑሮና ለስራ ምቹ አካባቢ ተፈጥሮ ማየት፤

2.2 ተልዕኮ
የአካባቢ፣ ብዝሀ-ሕይወትና የደን ሃብት አያያዝ፣ ልማትና አጠቃቀም ለዘላቂ ልማትና ለድህነት ቅነሣ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ሥርዓትን የማዘጋጀትና ተፈፃሚነቱን የማረጋገጥ፣ ምርምርና የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ሽግግርን የማስተባበርና የማካሄድ፣ ትምህርትና ግንዛቤን የማስፋፋት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ትግበራን የማስተባበር፣ የተግባሪዎችን አቅም የመገንባት፣ የደን ኢንቬስትመንትንና ግብይትን የማስፋፋት፣ ሀገሪቷ የተፈራረመቻቸውን ዓለም አቀፍ የአካባቢና የደን ስምምነቶች መተግበር እና ወቅታዊ የአካባቢ እና የደን ሁኔታና ለውጥ ዘገባን የማዘጋጀት ተግባራትን ያከናውናል፡፡
2.3 ዕሴቶች ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት በዕቅድ መመራት የተፈጥሮ ሀብትንና አካባቢያችን መንከባከብ የለውጥ ኃይሎችን ማበረታታት አሳታፊነት ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም ሙያዊ ሥነ-ምግባር ማስፋፋት ፍትሃዊነት ሰብአዊነት ተጠያቂነት ለአገር በቀል እውቀት እውቅና መስጠት የሴቶችና የወጣቶች የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መረጃን ለልማት ማዋል

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo