ከሁሉ አስቀድሜ በአስቸጋሪና ዉስብስብ ፈተና ውስጥ በጽናት በማለፍ በሀገራችን የተጀመረዉ የለውጥና የብልጽግና ጉዞ ለመላዉ ኢትዩጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለከተማችን ህዝቦች ያመጣቸዉን እጅግ አጓጊ የለዉጥ ትሩፋቶችና የፈነጠቀዉን ተስፋ ይበልጥ ለማስቀጠል ፀጋዎቻችን በመለየት ይበልጥ መስራት ይጠበቅበናል ። በተለይም ብዙ ዋጋ የከፈልለትን ለውጥ በምንም አይነት መንገድ እንዳይቀለበስና የሁለተናዊ ብልፅግናችን ጉዞ እንዲሳካ የበኩላችንን ያልተቆጠበ ድጋፍ በማድረግ እና እንደ ከተማ አስተዳደርም የተጀመረውን ሁሉ አቀፍ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ለህዝባችን ቃል የገባንባቸዉ የፖለቲካ፤ የማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤የመልካም አስተዳደርና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች እዉን ለማድረግ መላዉ የከተማችንን ሕዝቦችና የልማት ኃይሎች በማሳታፍ፤ በማስተባበርና በማቀናጀት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል እንደሚታወቀው ወልቂጤ ከተማ እረጅም እድሜ ያላት፤ብዙ የተፈጥሮ ፀጋዎች የተለገሰች ከምንም በላይ ጥረው ግረው ከምንም ተነስተው መልማት፥መበልፀግን ስራ ባህላቸው የሆነው በሀገራችን ለንግድ ስርዓት ውስጥ ጉልህ ሚና በመጫወት የሀገር ኢኮኖሚ በማቅናት የሚታወቁ የማህበረሰብ ክፍሎች የመሰረታት ከተማ ነች። ይሁን እንጂ ወልቂጤ በእድሜቿ ልክ ያላደገች፤ ያለማች ከተማ ሆና ቆይታለች የዚህ መሰረታዊ ምክንያቶች አንዱ እና ዋነኛው አብዝተው የኢትዮጰያ ሁለተናዊ ለውጥ በመሻት በባለፉት ስርዓቶች አብዝታ ተቃውሞ ስታቀርብ የስራዓቶች ሀሳብ ሀገር አሸጋሪ እንዳልሆኑ ሲሞግቱ የነበሩ ህዝቦች የነበሩባት በመሆኑ እልፍ አመታቶች በተለያዩ ሁኔታዎች ስትደቆስ እና በፖለቲካ ስራዓቱና በልማቱ ስትጨቆን ዘመናት ያለፈባት ከተማ በመሆና ምክንያት ሲሆን ሌላኛው ተወላጆች በከተማ ዙሪያ ያሉ ፀጋዎች አይናቸው ገልጠው ባለማየት የመልማት ትኩረታቸው በመንፈጋቸው ምክንያት በዋናነት መጥቀስ ይቻላል። የሆነው ሆኖ ወልቂጤና ህዝቦቿ ብዙ ዋጋ የከፈሉለትን ብዙ ዉጣውረድ ያየበት ለውጥ በእጃቸው ከወደቀ ወዲህ ገዥ መንግስት የሚያወርዳቸው የልማት ኢኒሼቲቭ የከተማ የማልማት ሀሳቦች በቅጡ በመገንዘብ እና በትክክልም የወልቂጤ የልማት ትንሳኤ የሚያረጋግጥበት ወቅት አሁን መሆኑን በመገንዘብ ህዝባችን ከመሪዎቹ በመቀናጀት ሀብት ያለው በሀብቱ፤ ሀሳቡን እና ጉልበቱን ሳይሰስት በመስጠት በከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ ውሰጥ መሆናችን እሙን ነው ከተማችን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች መገኛ በርካታ እንግዶች የሚያርፍባት እና የሚተላለፉባት ከተማ እንደ መሆና በርግጥም የህዝቦⶇ እና የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ማድረግ የሚችል ልምድ ያለው ስራ ባህሉ የሆነ ማህበረሰብ እና የተፈጥሮ ፀጋ ያላት ከተማ መሆና ለኢንቨስመንት ምቹ የሆነች እምቅ የተፈጥሮና የንግዱ አቅም ከፍተኛ መሆኑንን፤ ምድሩ ለምለም፤የዋቤ ወንዝ ለቱረዝም መስህብ አገልግሎት ሊውል የሚችል ያላት ፤ ምቹ አየርና የተፈጥሮ ፀጋ የታደልን ፣የሰው ኃይል በበቂ ሁኔታ መኖሩ፣ለስራ ታታሪ ህዝብ ባለቤት መሆኗ ተመራጭ ያደርጋታል ፡፡ ወልቂጤ የብልፅግና ተምሳሌት ማድረግ የሚቻልበት እድል ሰፊ ነው ደግሞም ትሆናለች ሁሉም ተወላጆች በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭ ያለችሁ አልሚ ባለሀብቶች የእናተን መምጣት ትጠብቃችሀለች እኛም አመራሮች ስትመጡ የተንቢ ብለን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንግኛለን። ኑ ወልቂጤ ከሁሉም ቀድማ የብልፅግና ተምሳሌት ከተማ እናርጋት!!!!!
በከተማው ሰላምና ፀጥታ ተረጋግጦ እና መልካም አስተዳደር ሰፍኖ ዘላቂ ልማትን በማምጣት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፡፡
በከተማው ያሉትን ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ ሐብቶች አቀናጅቶ፣ ቀጣይነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲዉሉ በመምራትና በማረጋገጥ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እድገትን አጠናክሮ በማስቀጠል የከተማው ህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ፡፡
• የህግ የበላይነት መርሀችን ነው፡፡
• ለተገልጋይ ፍላጎት ትልቅ ዋጋ እንሰጣለን፣
• መቻቻል ባህላችን ነው፣
• አሳታፊነት መለያችን ነው፡፡
• ፍትሐዊነትና ሚዛናዊነት መመሪያችን ነው፡፡
• ልዩነታችን ውበታችን፣ ውበታችን አንድነታችን ነው፡፡
ከድረገጻችን በተጨማሪ ዜናዎቻችን በፌስቡክ ገጻችን እና የቴሌግራም አድራሻችን መከታተል ይችላሉ።
የወልቂጤ ከተማን ከ 1998 ዓ.ም ጀምሮ ያስተዳደሩ ከንቲባዎች
© 2023 የድረገጹ መብት ለወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የተጠበቀ ነው። | በሄክስ ላብስ የበለጸገ።