የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ከወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በጋራ በመሆን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መርሀ ግብር ለ2ኛ ዙር በዛሬው እለት መክፈቻ አደረገ።

ህዳር 19/3/17(ወልቂጤ)

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ከወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በጋራ በመሆን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መርሀ ግብር ለ2ኛ ዙር በዛሬው እለት መክፈቻ አደረገ።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲን አቶ አጅመል መሀመድ እንደገለጹት የኢትዮ ኮደርስ ሰልጠናው ከዚህ ቀደም ለመምህራን መሰጠቱንና አሁን ለ2ኛ ዙር በኮሌጅ ላሉ የአስተዳደር ሰራተኞች ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ መጀመሩን ገልጸዋል ።

ስልጠናው እንደ ሀገር በተነደፈው መሰረት በተቋማችን የሚገኙ ከ300 በላይ የአስተዳደር ሰራተኞች ቴክኖሎጂውን አውቀው አሁን እየሄድንበት ያለውን የቴክኖሎጂ ስርዓቱ አውቀው በማሳወቅ ለሀገር ብሎም ለከተማው እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት አለባቸው በሚል ስልጠናው እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

የስልጠናው አድማስ በዚህ የሚገደብ ሳይሆን በቀጣይ ለተማሪዎች ና ሌሎችም መሳተፍ ለሚፈልጉ አካላት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው ስልጠናው መሰረታዊ ና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ሆኖ ለወጣቱ በነጻ እየተሰጠ ስለሚገኝ ይህን ትልቅ እድል በተገቢው መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል ።

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናው የሚወስዱ ሰልጣኞች መካከል በዘርፉ በቂ እውቀት የሚያገኙ ወጣቶች ከፍተኛ ክፍያ በሚያስገኙ የቴክኖሎጂ ና ፈጠራ ስራዎችን በመጠቀም ገቢያቸውን ከማሳደጋቸው በላይ የተሟላ የዲጅታል ክህሎት በመጨበጥ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን አጋዥ መሆኑን አቶ ሀምዱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ተናግረዋል ።

ቴክኖሎጂ የስራ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን የለውጥ አራማጅ የሆነበት አዲስ የዘመን ምዕራፍ ላይ ስለደረስን ወጣቶቻችን የኮዲንግ ክህሎት እንዲኖራቸው ስናደርግ ሰፊ ወደሆነው የዲጂታል አለም በልበ ሙሉነት በመቀላቀል በቀጣይ አገርን የሚጠቅምና የሰውልጆችን ህይወት የሚያቀሉ በርካታ አፕልኬሽኖች መፍጠር እንዲችሉ ይረዳል ብለዋል።

የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ክፍል ተጠሪ የሆኑት አቶ አመሀ አለማየሁ እንደገለጹት ስልጠናው በበይነ-መረብ የሚሰጥ ሲሆን የዛሬው ማስጀመሪያ በአካል የተደረገበት ምክንያት የሚሰለጥኑባቸው መስኮች በባለሙያ ድጋፍ ለይተው በመቀላቀል በቀጣይ ጊዜያት በእጅ ስልካቸው ስልጠናው እየወሰዱ ክትትልና ምዘናዎችን ተመዝነው ለሰርተፈኬት እንዲበቁ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የኢትዮ – ኮደር ስልጠና ሰዎች ከቴክኖሎጂ ተነጥለው ስራ ሊሰሩ ስለማይችሉ ሁሉም በየዘርፉ በቴክኖሎጂ በመሰልጠን ከስራቸው አስተሳስረው አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን አጋዥ በመሆኑ ስልጠናውን ተከታትሎ ሰርተፍኬቱ መያዙን አስፈላጊ እንደሆነና ስልጠናውን በተከታታይነት መውሰድ እንዳለባቸውም ሲሉ አመላክተዋል።

Previous ህዳር 18/2017ዓ.ም [ወልቂጤ ]

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo