ህዳር 18/2017ዓ.ም [ወልቂጤ ]

ህብረ ብሄራዊነት በሚያጠናክሩና የጋራ ልማትና እድገት በሚያፋጥኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ ።

የ19ኛ የኢትዮጵያዊ የብሄር ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ -ብሄራዊ አንድነት ” በሚል መሪ ቃል ቃል በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

በክብረ -በዓሉ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ህብረብሔራዊ ፌዴራል ስርዓት በኢትዮጵያ ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ ሀሳቦቹ በሚል የተዘጋጀ ሰነድ ለታዳሚያን ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ክብርት ፈሰሰወርቅ ገ/ሰንበት እንደተናገሩት ህብረ ብሄራዊነት በሚያጠናክሩና የጋራ ልማታችን ሊያፋጥኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ፈጥረን ልንሰራ ይገባል።

ተግባቦት ከቤተሰብ ይጀምራል ያሉት አፈ-ጉባዔዋ የሚፈጠሩ የሀሳብ ልዩነቶች በሰለጠነ መንገድ በውይይት በመፍታት ችግሮች ሲፈጠሩ የመፍትሔ መንገድ በመፈለግ በጋራ ሊያስጠቅሙን በሚችሉ ጉዳዮች መግባባት መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።

ህፃናት የሀገር መሰረቶች በመሆናቸው ይህም ክብረ በዓል በከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እየተከበረ መምጣቱን ገልፀው በሁሉም አደረጃጀቶች ስለ ብልፅግና ፣ወንድማማችነትና እህትማማችነት ፣ ሰላምና አንድነት እንዲሁም ሀገራዊ ለውጥና እድገት ላይ ንቁ ተሳታፊ ትዉልድ መፍጠር በሚያስችሉ ተግባራት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባረክ ዘይኑ እንደተናገሩት በዓሉ ከማክበር ባለፈ ልንኖርበት ይገባል ብለዋል።

ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማፅናት ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር ሁላችንም አንዱ የአንዱን ቋንቋ ፣ባህል፣ ታሪክና እሴትን ትውውቅ በማድረግ ልንማማርበት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ራሳችንን ከግጭት አጀንዳዎች በማራቅ የወል ትርክቶች ሀገራዊ መግባባት መሰረት በሚጥሉ ስራዎች በተጨባጭ መሬት አውርደን በጋራ ለልማትና ለለውጥ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ እንደገለፁት ሀገራዊ መግባባት ስንል የሀይማኖት ብዝሀነት፣የብሄ ር ብዝሀነና የቋንቋ ብዝሀነት አምነን ተቀብለን የምንፈልገውን የልማትና የብልፅግና ጉዞ ማሳካት ስንችል ነው።

ሁሉም በያለበት ዘርፍ ለአካባቢው ሰላምና ፀጥታ መስፈን ባለቤት ሆኖ ማገዝ ሲችል ነው ያሉት አቶ ታደለ እኩልነትና አንድነት በማጠናከር አብሮ የመኖር እሳቤን በማጎልበት በልማትና በመልካም አስተዳደር ለሚመጡ ለውጦች ማህበረሰቡ ባለቤት በመሆን ሊያግዝ ይገባል ብለዋል።

በክብር በዓሉ የተሳተፉ አካላት በሰጡት አስተያየት ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል መከበሩ ህብረብሔራዊ አንድነትን በማሳደግ የእርስ በእስር ባህልና እሴት ትውውቅ ለመፍጠር ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ መርህ የሆነውን አካታችነትና አሳታፊነት ማሳያም ነው ሲሉ ተሳታፊዎች አንስተዋል።

ልዩነቶችን እያጠበብን እንደ ሀገርና ከተማ ከኛ ምን ይጠበቃል በሚል እሳቤ ያሉን አደረጃጀቶችና ክበበባት በአግባቡ ተጠቅመን የሰላሙ ባለቤት እንዲሆኑ የማስቻል ስራ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

Previous የከተማውን ሠላም በማስጠበቅ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ውጤታማነት የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ገለፁ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo