የከተማውን ሠላም በማስጠበቅ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ውጤታማነት የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ገለፁ።

የከተማውን ሠላም በማስጠበቅ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ውጤታማነት የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ገለፁ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዙር 12ኛ አመት 43ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሂዷል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ክብርት ወይዘሮ ፈሰሰወርቅ ገብረሰንበት ምክር ቤቶች የዴሞክራሲ እና የሉዓላዊነት መገለጫ እንደመሆናቸው ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ይሰራሉ።

በዚህም የአስፈፃሚ አባላትን የስራ አፈፃፀም በመገምገም ችግሮች ተቀርፈው ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ክትትል ይደረጋል በማለት ይህ ተግባሩ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ጠቁመዋል።

በጉባዔው የበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በተሰሩ ስራዎች ውስንነት ቢኖሩም ከዕቅድ አፈፃፀም አንፃር የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም ክፍተቶችን በመለየትና ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የተሻለ ስራ ለመስራት ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

በተለይም የከተማውን መገለጫ የሆነው የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የተሻለ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ከንግግር ያለፈ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ብዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እያሉበት አብዛኛውን በጀት ለክለቡ እያዋለ ቢሆንም ክለቡ ካለበት ዕዳ አንፃር በከተማ አስተዳደሩ አቅም ብቻ መሸፈን ስለማይቻል የምክር ቤቱ አባላትን ጨምሮ ሌሎችም አካላት ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

እንደ ክቡር ከንቲባ ገለፃ የውዝፍ ብድር አመላለስ ላይም ችግር መኖሩን ጠቅሰው በዚህም ምክንያት በከተማው በሚፈለገው ልክ ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር አለመቻሉም ገልፀዋል።

በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የተናገሩት ክቡር ከንቲባው ውጤታማ እንዲሆንም የህዝብ ዕንደራሴው በቁርጠኝነት ሊደግፍ ይገባል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ በከተማው ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ በማድረግና አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንዲጀመሩ አትኩሮ በመስራት ከተማ አስተዳደሩ የቱሪዝም ኮንፈረንስ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

የከተማውን ሃብት በመጠቀም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች የከተማውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከመላው አመራርና ህብረተሰቡ ጋር በመሆን በቅንጅት እንደሚሰራም በጉባዔው ገልፀዋል።

ይሁን እኖጂ በከተማው ሊሰሩ የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በውጤታማነት የሚሰሩት በከተማው ሠላም ሲሆን መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተው ገልፀዋል።

በተለይም የከተማውን ሠላም ለማደፍረስ ፀረ-ሠላም በሆኑ አካላት ላይ ማህበረሰቡ ክትትል ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።

በከተማው የሚገኘው የፀጥታ ሃይል የከተማውን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ነው ያሉት ክቡር ከንቲባው ህብረተሰቡ ከነዚሁ የፀጥታ ሃይል ጎን በመሆን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

በዋናነት በከተማው ሠላም በማስጠበቅ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ውጤታማነት የምክር ቤቱ አባላት ጠንካራ ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ ድጋፋቸውን አጠናክሮ መቀጠል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በተጨማሪም ማህበረሰቡ ሲገበያይ ደረሰኝ የመጠየቅ ልምድ ማዳበር እንደሚጠበቅበትም ተናግረዋል።

የወባ ወረርሽኝ በመከላከሉ ረገድ ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣ የፋይናንስ የግዢ ስርዓት ማስተካከልና የኦዲት ስርዓት ማጠናከር፣ ሳምንታዊ ገበያ አጠናክሮ ማስቀጠል፣ ህገ-ወጥ የቤንዚን ችፍቼ ሻጮች ላይ ቁጥጥር ማድረግና እንዲሁም የከንቲባ ችሎት ማጠናከር እንደሚገባ የምክር ቤቱ አባላት አንስተዋል።

የተማሪዎች ውጤት ማሻሻል፣ የመሬት ወረራን መከላከል፣ የከተማው የትራንስፖርት የታሪፍ ክፍያ አላግባብ መጨመር፣ የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት መስጠት፣ የከተማው ሠላምና ፀጥታ ማስከበር፣ የከተማውን ወሰን ማስከበር፣ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ህዝባዊ ማድረግ፣ ለኢንቨስትመንት የተወሰዱ ቦታዎች በተገቢው አለማልማት፣ የመድኃኒት እጥረትና የማዐጤመ አገልግሎት አሰጣጥ ችግር እና ሌሎችም አስተያየቶችና ጥያቄዎች ከምክር ቤቱ አባላት ተነስተው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

የ2O17 ዓመተ ምህረት የዩ አይ አይ ዲፒ [UIIDP] የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በከተማው ማዘጋጃ ጽህፈት ቤት ሃላፊ በአቶ ይብጌታ ንጋ ቀርቦ ውይይት በማድረግ በምክር ቤቱ አባላት ፀድቋል።

ጉባኤው በውሎው በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የቀረቡለትን ሹመቶችን ያፀደቀ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ በ2O17 በጀት አመት ጠቋሚ ዕቅድ ላይ ከከተማው ምክር ቤት ጋር በመፈራረም ተጠናቋል።

Previous ”የሃሳብ ልእልና ለሁለንትናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ አመት ክብረ በዓልን በማስመልከት በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተካሂዷል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo