የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት በከተማው የሚገኙ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በዛሬው እለት የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ማስጀመሪያ አደረገ።

ነሀሴ 9/2017ዓ.ም [ወልቂጤ ]

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት በከተማው የሚገኙ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በዛሬው እለት የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ማስጀመሪያ አደረገ።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀምዱ ካሚል እንደገለጹት መንግስት 5 ሚሊዮን ዜጎች ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰድ እንዲችሉ ከአረብ ኤምሬት ጋር ውል ስምምነት ገብቶ እድሉ ሲያመቻች አለም በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያሳየች ባለው ምጥቀት በሀገራችንም በቴኖሎጂው አብሮ የዘመነ ወጣት ለመፍጠር አላማን አንግቦ ለመስራት ነው ብለዋል።

ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ለፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ስርቆቶችን በቴክኖሎጂ በመታገዝና በመቆጣጠር ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

ስልጠናው አራት ኮርሶች መኖራቸውን ገልጸው በነዚህ ስልጠናዎች አለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፍኬት በመያዝ አገልግሎት አሰጣጣችን ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ በባንክ ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን በመቆጣጠር ከቴክኖሎጂው ጋር ተወዳዳሪ መሆን ያስፈልጋል ሲሉ ሀላፊው ጠቁመዋል።

የጆካ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ጀማሉዲን ከማል በበኩላቸው የዲጂታሉን አለም ምሰሶ ሆኖ የሚያገለግለው የቴክኖሎጂው ዘርፍ እድገት ጋር አብሮ መዘመን ከተቋሙ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አውስተው በመንግስት ኢኒሼቲቭ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በመጀመራቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ስራ አስኪያጅ አክለውም ስልጠናውን ወስደው ሰርተፍኬቱን ሲይዙ ተጨማሪ እውቀትና ክህሎት በማግኘት በባንክ አሰራር የሚገጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ለመከላከል እንደሚያግዝም ተናግረዋል።

Previous ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ማህበረሰቡን በቴክኖሎጂ የተደገፈ እውቀትና ክህሎት ከማሳደግ ባሻገር የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo