የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የእርዳታ ማህበራት በከተማው ውስጥ የሚሰሩ የልማት ስራዎች በመደገፍናን የኢኮኖሚ ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ጥረት ቁልፍ ሚና አላቸው ፦የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ገለጸ።
ጥር 15/2018ዓ.ም[ወልቂጤ ]

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት የመንግስት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የጋራ የምክክር መድረክ አካሄደ።
የምክክር መድረኩም በስራ ላይ ከሚገኙ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር የመግባብያ ስምምነት ተፈራርመው በስራ ላይ የሚገኙ መሆናቸውና ባለፈው አመት የተሰሩ ስራዎች በበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል ።
መንግስት በከተሞችን የጀመረውን ፈጣን ልማት የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተሳትፎ በተከታታይነት ለማሳካት ካለው ፍላጎት አንፃር የበጎ አድራጎት ማህበራት ሁለንትናዊ ተሳትፎ ሲያበረታታና ሲደግፍ መቆየቱ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ እንዳለ ጥዩ ገልጸዋል።
የልማት ስራው በመደገፍ ቁልፍ ሚና ከሚጫወቱት የልማት ሀይሎች መካከል ልማታዊ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በከተማው ውስጥ ከፍተኛ መዋእለንዋይ በማፍሰስ እውቀትና ልምድ በማካፈል የኢኮኖሚ ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ጥረት አበረታች ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

እነዚህ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የከተማውን ችግር ከመቅረፍ አንፃር በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ስለሆነ ምቹ ሁኔታዎች ቢኖራቸው ደግሞ ከዚህ የበለጠ ስራ ሊሰሩ ስለሚችሉ ሁሉም ባለድርሻ አካል የድርሻውን ወስዶ እንደሚያግዝም ሀላፊው አብራርተዋል።
በከተማችን ውስጥ በሀብታቸው በመደገፍ፣ እውቀትና ልምዳቸው በማካፈል እንዲሁም የተቸገሩትን በመርዳት የሚያደርጉት ሁለንተናዊ ተሳትፎ እጅግ ሚበረታታ ነው ሲሉ የገለፁት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ ነኢማ አክመል ናቸው።

አክለውም በከተማው 8 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መገኘታቸውን ገልፀው ሚስተዋሉትን የመንግስት የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ጉልህ ሚና እንዳለው አመላክተዋል።

በምክክር መድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የወልቂጤ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ መንዚላት አህመድ በበኩላቸው ከተማው ላይ መንግስት ላደረሰባቸው የማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል።
ክብርት መንዚላ አያይዘውም በኢትዮጲያ ሴቶች ማህበር በጤናው ዘርፍ በሴቶች ላይ የተጀመሩ የቅድመ-ምርመራ ስራዎች በማስቀጠል ጤናቸው የተጠበቁና ጤናማ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ ከተረጂነት ለማላቀቅ በቆይታቸው የቁጠባ ባህልን በማለማመድ አቅም ፈጥረው ወደሌላ ተጠቃሚ መሸጋገር መቻል አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

በምክክር መድረኩ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት በአስተያየታቸው የበጎ አድራጎት ማህበራቱ በከተማው በህረተሰቡ ተጠቃሚነት ላይ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸው በሚሰጡ ስልጠናዎች መነሻነት ከተረጂነት ለመውጣት ወደ ሰራ እድል በመቀየር ከተረጂነት የሚላቀቁበት መንገድ ሊፈጠር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።
የበጎ አድራጎት ማህበሮቹም ዳይሬክተሮች በሰጡት አስተያየትም እንደገለጹት በመንግስት በኩል ሊታገዙ የሚገቡ ጉዳዮች ወስዶ በመተጋገዝ የተሻለ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩም አንስተዋል ።
ከተረጂነት ወደ ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በድርጅቶቹ በስልጠናዎች አቅም በመፍጠር መነሻ ስራዎች የመስራት ስራ እንደሚሰሩም አንመላክተዋል።
ትምህርት ላይ ውጤታማነት ለማምጣት የሁሉም ባለድርሻ አካል ርብርብ ስለሚጠይቅ ሁሉም የድርሻውን በመተጋገዝ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋን መፍጠር ይገባል ብለዋል።

