የጥምቀት በዓልን ስናከብር የምናሳየው ደግነት፣ ፍቅር፣ ትህትና እና አክብሮት የዘወትር ስራችን ሊሆን ይገባል ሲሉ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሃገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ሉቃስ አስገነዘቡ።

የጥምቀት በዓል በጉራጌ ዞን መዲና በወልቂጤ ከተማ እንዲሁም በጉብርየ ክ/ከተማም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡

ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም [ወልቂጤ]

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ የመረዳዳት እና የመደጋገፍ እንዲሁም የአብሮነትና የመተሳሰብ እሴቶችን ማጎልበት እንደሚገባም ተገልጿል።

የጥምቀት በዓል በሀገራችን በድምቀት ከሚከበሩ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን ይህም በመላው በሀገሪቱ ክፍሎች በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በየአመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ መልከጼዴቅ፣ በአሉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት በዛሬው እለት በመላው የሀገራችን ክፍሎች ላይ እየተከበረ የሚገኘው የጥምቀት በኣል ልዩ ትርጉም ባለዉ መልኩ እየተከበረ ይገኛል።

በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ይህም በኣል ስናከብር ሃይማኖታዊ ስርዓቱንና አስተምሮን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበትም ገልጸዋል ፡፡

አቡነ መልከጼዴቅ እንደሚገልጹት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሚከበሩት ብሄራዊ በአላት መካከል የጥምቀት በአል አንዱ መሆኑን ገልጸው ይህም ከብሄራዊነት አልፎ በአሁኑ ሰአት በአለም ከማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ በመሆኑ ይህን በመጠበቅና ለአለም ይበልጥ በማስተዋወቅ የቱሪዝም ሀብትን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተለይም አሁን ላይ እንደ ሀገር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአንድነት የምንቆምበትና ጥላቻ፣ መገፋፋትአ እና መገደዳልን በመተው የእርስ በርስ ግንኙነታችንን የምናጠናክርበት ወቅት ላይ እንገኛለንም ብለዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ በባዓሉ ተገኝተው ባደረጉበት ንግግር የጥምቀት በዓል በሀገራችን ብሎም በዞናችን በድምቀት የሚከበር ታላቅ የአደባባይ በዓል እንደሆነ ገልጸዋል።

የጥምቀት በዓል የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት በዓል በመሆኑ አብሮነትን፣ መቻቻልን በማጎልበት ኢትዮጵያዊነት ከፍ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ ላጫ አክለውም በኣሉ ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ የሚከበር በመሆኑ ይህም በውስጡ የያዘው መስህባዊ እና ተፈጥሯዊ ውበት ምክንያት በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች የሚሳተፉበት በኣል በመሆኑ መጠበቅና ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አያይዘውም አሁን ያለው የብልጽግና መንግስት የጀመረው የህዝቦችን አንድነት እና መተባበርን አጠናክሮ በማስቀጠል የዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና ከማረጋገጥ ባለፈ ለህዝቦ ክብር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና የተራቡትን በማብላት መሆን እንዳለበትም አቶ ላጫ ገልፀዋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በበኩላቸው የጥምቀት በኣል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት ውስጥ አንዱና ግንባር ቀደም እንደሆነ ገልጸው ለዚህም ምክንያቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በዩርዳኖስ ወንዝ በቅዱስ ዩሀንስ እጅ የተጠመቀበትን እለትን በማስታወስ በምእመናኑ ዘንድ ልዩ ትርጉም የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።

አክለውም ጥምቀት ኢየሱስ ክርስቶስ በሠው ልጆች ሀጢያት ምክንያት በዩርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀበትን ታሪካዊ ክስተት ለማሰብና ለሃጥያት ምህረትን በማድረግ የመንፈስ ቅድስ መገለጥ የሚቀኝበት እንደሆነም አቶ ሙራድ ጠቁመዋል።

ወልቂጤ ከተማችን ረጅም እድሜና ታሪክ ያላትና ብዙ የተፈጥሮ ጸጋ የተቸራት የታታሪዎች የሰላምና ስራ ወዳዶች ከተማ መሆኑዋን የገለፁት አቶ ሙራድ በከተማ አስተዳደር ውስጥ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለበዓሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱበት በመሆኑ ይህን መልካም እሴት ይበልጥ ሊጠናከርና ለሌላው አካባቢ አርዓያ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ከንቲባው አያይዘውም መላው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ የመረዳዳት እና የመደጋገፍ እንዲሁም የአብሮነትና የመተሳሰብ እሴቶችን በማጎልበት ሊሆን እንደሚገባው ተገልጿል።

በመጨረሻም አቶ ሙራድ በከተማው የሰላምና የልማት ጉዳይ እንዲሁም ለዛሬው ለበአሉ መሣካት ከፍተኛ ሚና ስለነበራቸው አባቶች፣ ወጣቶች አመራሮች የከተማው ነዋሪዎች እና ሌሎችም በየደረጃው ለሚገኙ አካለት ምስጋና አቅርቧል።

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባረክ ዘይኑ በጉብርየ ክፍለ ከተማ በዓሉን በታደሙበት ወቅት እንደገለፁት የጥምቀት በዓል ፍቅር ሠላምና ትህትና የተገለፀበት እንደ መሆኑ የጥምቀት በዓልን ስናከበር ኃይማኖታዊ አስተምህሮውን በጠበቀ፣ ማህበራዊ ትስስራችንንና አብሮነታችንን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በማከናወን ፣ በፍቅር ፣ በሠላም፣ ለተቸገሩ ወገኖች ካለን በማካፈል፣ በመተሳሰብ ስሜትና ተግባራት የምናከብረው ሊሆን ይገባል ያሉ ሲሆን

‎

‎በከተማዋና በሀገሪቱ እየተከናወነ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ አስመልክቶ በስፋት የተናገሩት አቶ ሙባረክ አሁንም በቀሪ የልማት ስራዎቻችን ማህበረሰቡ የነበረው ጥንካሬ ሊያስቀጥል ይገባልም ብለዋል።

Previous በአዳሪ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሰራተኞች በአንድነት በዓሉ ቤተሰባዊ ፍቅርንና አንድነትን በጠበቀ መልኩ እንዲያሳልፉ አስፈላጊ ዝግጅቶች መደረጉም ጠቁመዋል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo