ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት “በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት “በሚል መሪ ቃል አመታዊ የጤና ጉባኤ አካሄዳ ።

‎ጥቅምት 15/2018ዓ.ም (ወልቂጤ )

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት “በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት “በሚል መሪ ቃል አመታዊ የጤና ጉባኤ አካሄዳ ።

‎ጥቅምት 15/2018ዓ.ም (ወልቂጤ )

‎በጤና ጉባዔ ላይ የ2017በጀት አመት በተቋሙ የተከናወነው ተግባራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት በ2017 በበጀት አመት በጤናው ዘርፍ የተመዘገበው መልካም አፈፃፀም በማሳደግ የተስተዋሉ ክፍተቶችን እየለዩ ማረም ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።በጤናው ዘርፍ በማህበረሰቡበ በተደጋጋሚ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ለመመለት ከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን አስረድቷል።የተሻለ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰባችን ተደራሽ ለማድረግ በሽታን ቅድመ የመከላከል ስራዎች በማጠናከር፣የጤና ልማት ሰራዊት መፍጠር፣በጤና ተቋማት ጠንካራ የእርስ በእርስ ግኑኝነት በማጠናከር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ገልፀዋል።ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ከመከላከል አንፃር በርካታ የሚጠበቁብን ተግባራ በመኖራቸው በማህበረሰባችን ላይ የግንዛቤ ስራዎች በማስፋት እና ለምንሰጠው አገልግሎት ጥራት በሀላፊነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ እንደተናገሩት አምራች ዜጋ ለመፍጠር ጤናውን የተጠበቀ ማህበረሰብ መፍጠር ስለሚገባ በጤናው ዘርፍ የተጀመሩ አበረታች ውጤቶች ሁሉም በቅንጅት በመስራት ሊያስቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

‎በከተማችን በከፋተኛ ፍጥነት የጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ስርጭት ለመከላከል በሁሉም ቀበሌዎች ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋትና አደረጃጀቶች በማጠናከር ቅድመ የመከላከል ስራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።‎ህብረተሰቡ በጤናው ስራ ንቁ ተሳታፊ በማድረግ በተለይ በማህበረሰባችን ዘንድ መዘናጋት የሚታይበትን የኤችአይቪ ኤድስ በሽታን የግንዛቤ ስራዎች ከሌላ ጊዜ በተሻለ ሊሰራ እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን ህብረተሰቡም የራሱን ጥንቃቄ በማድረግ ሊያስተምር እንደሚገባም አሳስበዋል ።

በከተማው የሚገኙ ጤና ጣቢያቸው በራሳቸው አቅም ፈጥረው የገቢ አቅማቸው በማሳደግ ማህበረሰባችን የሚያነሳውን የጤና አገልግሎት ስርዓት ማሳደግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።

‎

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባረክ ዘይኑ እንደተናገሩት በበጀት አመቱ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ትኩረት ሰጥተን በመፈፀም አዲሱ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ በማነቃቃት ፣የወረርሽኝ መላከል እና አክሞ ማዳን እንዲሁም የቤተሰብ ጤና ቡድን የማጠናከር ስራዎች ውጤታ ካስመዘግብናቸው ተግባራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

በሽታን ቅድመ የመከላከል ስራዎች በማጠናከር ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ እና በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ስራዎች ከባለፉ አመታት ጥሩ መነቃቃት የነበረበት እንደነበረም አስረድተዋል።

በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የወባ በሽታ ስርጭት ከክረምት ወራት በኋላ ከመስከረም እስከ ህዳር በከፍተኛ ደረጃ የሚተላለፍ በመሆኑ የከተማው ማህበረሰብ በቅድመ የመከላከል ስራ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

‎በቀጣይ የጤና ተቋማት የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች በማጠናከርና የማህበረሰብ ተሳትፎ በማሳደግና የጤናው ባለቤት በማድረግ ለሚከናወኑ ተግባራት ሁሉም በባለቤትነት ሊመራና ሊያግዝ እንደሚገባ ጠቁመዋል።‎የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ኤደን አለሙ እንደተናገሩት በጤና አገልግሎት ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ለማጠናከር ሁሉም በሀላፊነት ሊያግዝ ይገባል ብለዋል።

‎ከተማ አስተዳደሩ ለጤና ጣቢያዎች ከግብዓት አቅርቦት ጀምሮ እየሰራ ያለው ስራ አበረታች በመሆኑ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።በወልቂጤ ጤና ጣቢያ በቤተሰብ ጤና ቡድን እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ለሌሎች ምሳሌ መሆን የሚችል በመሆኑ ጤና ጣቢያዎች የእርስ በእርስ ትስስር በመፍጠር ማህበረሰባቸውን በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸውም አንስተዋል።በጤና ጉባኤ ላይ የተገኙ አካላት በሰጡት አስተያየት ጤና የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ቅድመ የመከላከል ስራዎች ላይ ሁሉም በሀላፊነት ሊያግዝ እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎‎በበጀት አመቱ ለጤናው ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ሲሆን በተለይም የገጠር ቀበሌዎች ላይ የሚገኙ ጤና ኬላዎች ትኩረት እንዲሰጣቸውም አስተያየት ሰጥተዋል።

‎በመጨረሻም በ2017በጀት አመት በጤናው ዘርፍ ለተመዘገበው ውጤቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለተወጡ አካላት የሽልማትና የመስጋና መርሀ ግብር በማካሄድ መድረኩ ተጠናቋል ።

‎

‎

Previous በጎ ፍቃደኝነት ከዛሬም አልፎ ለነገ ህይወት የትርፋማነት ስንቅ በመሆኑ ወጣቶችና ባለሀብቶች ከመንግስት ጎን ሆኖ ለወገን መድረስ ይገባል:- አቶ አስራት ታደለ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo