በጎ ፍቃደኝነት ከዛሬም አልፎ ለነገ ህይወት የትርፋማነት ስንቅ በመሆኑ ወጣቶችና ባለሀብቶች ከመንግስት ጎን ሆኖ ለወገን መድረስ ይገባል:- አቶ አስራት ታደለ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ
ጥቅምት 16/2018ዓ.ም [ወልቂጤ]

የአብሽር በጎ አድራጎት ማህበር ከወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት በጋራ በመሆን ለአቅመ ደካማ ወገኖች የሻወር እጥበት፣ የአልባሳት ድጋፍና የምገባ መርሀ ግብር ተካሄደ።
በጎ ፍቃደኝነት ከዛሬም አልፎ ለነገ ህይወት የትርፋማነት ስንቅ በመሆኑ ወጣቶችና ባለሀብቶች ከመንግስት ጎን ሆኖ ለወገን መድረስ ይገባል ሲሉ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አስራት ታደለ ተናገሩ።
በከተማ ደረጃ የብልጽግና ፖርቲ ሰው ተኮር አላማን ከግብ ለማድረስ ድጋፋችንን ለሚሹ ወገኖች ዘርፈ ብዙ የበጎ ፍቃድ ስራዎች እየተሰራ መቆየቱን አስታውሰው በዛሬው እለትም በበጋው በጎፍቃድ አረጋዊያን ና በጎዳና የሚገኙ ወገኖችን የትጥበት የማልበስና የማዕድ ማጋራት መደረጉንም አስረድተዋል ።

የወልቂጤ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ቶፊቅ ጀማል በበኩላቸው በጽህፈት ቤቱ በበጋና በክረምት በጎ ፍቃድ ለማህበረሰቡ አገልግሎት መሰጠቱን ገልጸው በ2018 በጀት አመትም በበጋው በጎ ፍቃድ ከአብሽር በጎ አድራጎት ማህበር በመተባበር ለአቅመ ደካሞች ና በጎዳና ለሚገኙ ወገኖች የሻወር ትጥበት ፣የአልባሳት ድጋፍና ምገባ መደረጉም አመላክተዋል።
በቀጣይም ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል።
በከተማው የበጎ ፍቃድ ስራ ባህል እየሆነ በመምጣቱ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በየደረጃው የበኩሉን ሚና በመጫወት የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህሉን ማስፋት አለበት ብለዋል።

ማህበሩ በአመት አራት ጊዜከ200-300 ለሚደርሱ አረጋዊያንና በጎዳ የሚገኙ ወገኖች ትጥበት፣ ማልበስና ምገባ እያካሄደ በየ15 ቀኑ የቤት ለቤት ጥየቃ እያደረገ መቆየቱን የገለጸው ወጣት አብድልሰላም ሰይድ የአብሽር በጎ አድራጎት ማህበር ሰብሳቢ ነው።
በቀጣይ ይህ በጎ ፍቃድ ስራ ለማንም ተነጥሎ ለሚሰጥ ሳይሆን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ በማበርከት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ወጣቱ ተናግሯል።
ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከልም አቶ ተመስገን ወልዴና አቶ አብረሃም ዲጌቦ እንደገለጹት በተደረገላቸው ድጋፍ ድጋፍ መደሰታቸውንና መሰል ድጋፎች እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

