ታህሳስ 10/4/2017ዓ.ም (ወልቂጤ)

የማህበረሰብ አቀፍ ችግሮች ለመቅረፍ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች የጋራ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ተገለፀ።
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ዘቢደር ቢራ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በጋሶሬ ቀበሌ የትምህርትና የመብራት ሀይል ተደራሽነት ለማስፋፋት ያለሙ ፕሮጀክቶች አስመረቀ።
የእለቱ የክብር እንግዳና የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለፁት ቢጂአይ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ግዴታውን ለመወጣት እያደረገ ያለው ጥረት አመስግነው።

እንደ ሀገር የተቀመጡ ግቦች በመንግስት ብቻ ማሳካት ረጅም ጊዜ የሚወስድ እንደመሆኑ መጠን በትምህርት ቤት ልማታዊ ስራዎች የግል ባለሀብቶች ማሳተፍ አካባቢ በማልማት እንዲሁም ለደረጃ የሚመጥኑ የትምህርት ተቋማቶች እንዲገነቡ በማድረግ ወቅቱን የሚመጥን ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ነው ብለዋል።
አቶ ላጫ አክለውም የትኛውም ወላጅ የትኛውም ሰውኛ ባህሪ ያለው አካል ምኞትና ፍላጎት መሆን ያለበት በእውቀትና በስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ መቅረጽ ነው ብለዋል።

የብልጽግና መንግስት ፖሊሲዎችን ነድፎ ወደ ተግባር ሲገባ በማህበራዊ ዘርፉ ለውጦቹን ለማረጋገጥ ትኩረት ካደረገባቸው መስኮች መካከል ትምህርት መሆኑን የገለፁት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ሲሆኑ።
ትውልድ በአግባቡ ግብረ ገብነት ኖሮት፣ በእውቀት ታንጾ ነገ ሀገር ሊረከብ የሚችል አካባቢ ሊያለማ የሚችል ትውልድ መቅረጽ ያስፈልጋል ብለዋል።
አቶ ሙራድ አያይዘውም የጋሶሬ ትምህርት ቤት ረጅም እድሜ ያለውና ለብዙዎች ፊደል ያስተማረ ለሀገር የሚጠቅሙ በርካታ ምሁራን ያፈራ እንደመሆኑ መጠን ያለበትን የልማት ጉድለት ለማሟላት አጽንኦት በመስጠት የአካባቢ ችግር ለመፍታት አቅዶ ሰፊ ስራዎች እየሰራ ለሚገኘውና በዛሬው እለት 8 ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን በማስገንባቱ ቢጂአይ ኢትዮጵያ አመስግነዋል።

ትምህርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ የእድገት ስልጣኔ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እሴቶች መገንባትና ሀገራችን በተጨባጭ ሁኔታ ለሚጎናጸፋቸው ግብ መሳካት አይነተኛ ሚና የሚጫወት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን የገለፁት የወልቂጤ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ስሜነሽ ግርማ ሲሆኑ::
በሀገራችን ብሎም በአካባቢያችን ባሉ ትምህርት ቤቶች እየመጣ ያለው ውጤት እኛን የሚመስል ባለመሆኑ ተቋማቶቻችን ባላቸው የመማር ማስተማር ብቃት ተሻሽሎ ነገ የተሻለ ሀኖ ማየት ነው ብለዋል።
የቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ሴኤስአር ዳይሬክተር አቶ በኃሉ አየለ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ፣ በጤናና በአካባቢ ጥበቃ ስራ በርካታ ስራዎችን በመስራት ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንደሚገኝ ገልጸው።

በዛሬው እለት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 2 ብሎክ መገንባቱን አንስተው ይህም ከ6 መቶ በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር እንደሚችል አመልክተዋል።
አቶ በሀይሉ አክለውም ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የተዘረጋው የጋሶሬና አካባቢው የኤሌክትሪክ ሀይል 4 መቶ አባወራዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
ወጣት ኢንጅነር ሚስባ በበኩላቸው በግንባታ ወቅት ሲያጋጥማቸው ለነበሩ ጉድለቶች አፋጣኝ ምላሽ በማግኘታቸው ስራው እንዲሳካ አግዞኛል ብለዋል።
በስተመጨረሻም ለማስፋፊያ ግንባታው አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላቶች የማበረታቻ የምስክር ወረቀትና ሽልማት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

