
ህዳር 19/2017ዓ.ም (ወልቂጤ)
ለከተማ እድገት መፋጠን የመሰረተ ልማትና የህንፃ ግንባታ ስራዎች የላቀ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።
የወልቂጤ ከተማ እድገት ለማፋጠን ከመሬት ሀብትና ከህንፃ ግንባታ ስራዎች ጋር በተያያዘ የከተማ አስተዳደሩ ከከተማው ባለሀብት ጋር ውይይት አካሄደ።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ሙራድ ከድር እንደተናገሩት እንደ መንግስት የከተማ ልማት ማረጋገጥ የሚቻለው ወቅቱን የዋጀ ግንባታና የንግድ እንቅስቃሴ ሲኖር እንደሆነና በከተማችንም ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ ብልጽግና ሊረጋገጥ በሚችል መልኩ የተሰሩ ስራዎች መኖራቸውን አመላክተው ።
የአንድን ከተማ ሀብት ህዝብና መሬት ሆኖ ሳለ እንደናንተ ዓይነት ባለሀብት ያለባት ወልቂጤ ከተማ ባለሀብቱ የሚመጥንና የዘመነ ሆኖ አቻ ከተሞች የደረሱበት አለመድረሷ አስጨንቆን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
አቶ ሙራድ አክለውም ከተማዋ ተፈጥሮ ከለገሷት እድሎች መካከል ለኢንቨስትመንትና ለኮሪደር ልማት ምቹና ሰፊ የንግድ እንቅስቃሴ ያለባት እንደመሆኗ መጠን ከአቻ ከተሞች ጋር ስትነፃፀር በዚህ ልክ መሆኗን ሊያስቆጨን ይገባል ያሉ ሲሆን።
እኔና መሬቴ አብረን እንኑር ከሚል አሰተሳሰብ በመውጣት ከተማዋ በማልማት ጉዳይ ላይ የጋራ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊና የከተማ አስተዳደሩ ደጋፊ የሆኑት አቶ ታምራት ውድማ በበኩላቸው በከተማ መልማት ዙሪያ ባለሀብቱና የከተማው መንግስት በዚህ ልክ ተቀራርቦ መወያየቱ ትልቅ ግብዓት ነው ያሉ ሲሆን።
እንደ ከተማ በሊዝ የተወሰዱ መሬቶች ላይ ግንባታ ተጀምሮ ያልተጠናቀቀበትና ጅምር ላይ ሆኖ ከታች ስራ የተጀመረበት አግባብ ከተማዋ የማይመጥን ከመሆኑ አንፃር እርምት ሊደረግባቸው ይገባልም ብለዋል።
የኮንስትራክሽን ተግባር ለማነቃቃት መንግስት ችግሩን ተረድቶ በ2005ዓ.ም መሬት በሊዝ፣ በምደባና በራስ ይዞታ አልሚው እንዲያለማ በእቅድ የተሰራበት ነው ሲሉ የገለጹት የከተማው ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስራ አሰኪያጅ አቶ ይብጌታ ንጋ ሲሆኑ።
አዋጅና ስታንዳርድ መተግበር ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ በከተማ አስተዳደሩ ለልማት የተፈቀዱ ቦታዎች መልማት መቻል አለባቸው ብለዋል።

የከተማው ፓርቲ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጴጥሮስ አስራት እንደገለጹት በመንግሥት አሰራር መሰረት በዋናው መንገድ ተዘጋግተው የተቀመጡ የመንግስት ቤቶች በቃ ሊባሉ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊ ባለሀብቶች ሲገልፁት እንደነበረ ተጀምረው የቆሙ ህንፃዎች ለማስጨረስ የሚነሳሳ ባለሀብትና የግንባታው ሂደት የሚገመግም የመንግስት አካል በቅንጅት ከሰሩ ከተማዋ ትለማለች ያሉ ሲሆን።

ከተማዋ በከተሞች ህግና ደንብ መሰረት ማስተዳደርና ጉድለቶቻችን እንዲሟላልን በምንጠይቅበት ወቅት መንግስት አጋዥነቱን ሊያረጋግጥ ይገባልም ብለዋል።

በስተመጨረሻ አቶ ሙራድ ከድር ከውይይታችን በኋላ በቁርጠኝነት ወደ ስራ መገባት እንዳለበትና አቻ ከተሞች የደረሱበት ለመድረስ የአመራር ቁርጠኝነት እንዳለ ሆኖ የባለሀብቶች አጋዥነት በዋናነት የሚጠቀስ ነው በማለት መድረኩን አጠናቀዋል።

