ጥር 9/2017 ዓ.ም [ወልቂጤ]
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛውን የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ በወልቂጤ ከተማ ደረጃ ተካሂዷል ።

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የከተማ አስተዳደሩ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈትቤት ኃላፊ አቶ ታደለ በቀለ እንደገለፁት ፓርቲያችን ብልፅግና ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ በኢኮኖሚ፣ ፓለቲካና በማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልፀው ።
ብልጽግና የገባቸው ቃሎች ወደ ባህል በመቀየር ማጽናት እንዳለብንና ፓርቲው አይቻልምን በይቻላል የቀየረ ሀገራችንን ማሻገር የሚችል የሀሳብ ልዕልና ያለው ፓርቲ በመሆኑ ጉባኤው ውጤታማ የሆኑ ስራዎችን እውቅና የምንሠጥበት ክፍተቶቻችንን ደግሞ ለማረም የሚያስችለን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በማጠቃለያ ኮንፈረንሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወነው የለውጥ ስራዎች በቪዲዮ በክቡር ፕሬዝዳንቱ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በበኩላቸው ጉባኤው እንደ ሀገርና እንደ ከተማ ያገኘናቸውን ትልልቅ ድሎችንና ውጤቶችን አጠናክረን ለማስቀጠል በፓርቲና በመንግስት ቃል የምንገባበት ፤ የወጣቶችንና የሴቶችን ተጠቃሚነት የምናሳድግበት፤ የአርሶ አደር ስራን አጠናክረን የምንቀጥልበትና የህዝባችን ተጠቃሚነት የምናረጋግጥበትና ለፓርቲያችን ልዕልና በትኩረት የምንሠራበት ይሆናል ብለዋል።
አቶ ሙራድ አክለውም የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ኢትዮጵያዊ አብሮነትን የሚያስተሳስሩ በርካታ ስራዎችን በመስራት ችግሮችን መፍታት የቻለና ትልልቅ ፕሮጀክቶችን የሰራ ፓርቲ መሆኑን አመላክተዋል።
አንዳንድ የውይይቱ አካላቶች እንደገለፁት ብልፅግና ፓርቲ የሰራቸው በርካታ ተግባራት መኖራቸውን አንስተው ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የተጀመሩ ልማቶች በማፋጠን፣ የፓርቲ ተቋማት በማጠናከር እንዲሁም የኢትዮጵያ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከብልፅግና ፓርቲ ጎን እንደሚሰሩም ገልፀው ።
በከተማና በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ወደ ሚፈለገው ስኬት ለመቀየር አስፈፃሚው አካልና የፊት አመራሩ ለነዋሪው ማህበረሰብ አርዓያ መሆን አለባቸው ብለዋል።

የብልጽግና ጉዞአችን በተፈጥሮአዊና በሰውሰራሽ ችግሮች ውስጥ ሆና ፈተናዎችን ወደ ድል በመቀየር ለሁለንተናዊ የብልጽግና መረጋገጥ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ያመላከቱት የከተማው ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ሲሆኑ።
እቅዶችን በመከለስ፣ ጠንካራና ችግር ፈቺ ግብረ-መልስ በመስጠት፣ የአመራር ቁመናና ታማኝነት ሚዛናዊነት ያለው እንዲሆን ማድረግ፣ አደረጃጀቶች የመርሀግብር እንዳይሆኑ በማድረግና ህብረብሄራዊ አንድነታችን በማስቀጠል ስራዎች እንዲሰሩ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠው ።
በእያንዳንዱ በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ህግና አሰራር በጠበቀ መልኩ በተሰሩ ስራዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያም ሰጥተውበታል።
በስተመጨረሻም የቀጣይ የጉባኤ ተሳታፊዎችን በማስመረጥ ኮንፈረሱ ተጠናቋል ።

