የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት ቋንቋና ስነ-ጥበብ ለማሳደግ ሳይንሳዊ ስልቶችን በተከተለ መልኩ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመለየትና በማጥናት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ገለፁ።

ያለንን ባህልና እሴት መጠበቅና ማሳደግ አንዱ የስልጣኔ መገለጫ በመሆኑ ቋንቋችን እንዳይጠፋና በታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን ሁላችንም የድርሻችንን ወስደን አሁን የተጀመሩ መልካም እንቅስቃሴዎችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ቋንቋና ስነ-ጥበብ ለማሳደግ ሳይንሳዊ ስልቶችን በተከተለ መልኩ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመለየትና በማጥናት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ ።

ጥር 1/2017 ዓ.ም (ወልቂጤ )

የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት በጉራጊኛ ቋንቋ እና ኪነ ጉራጌ ላይ የተዘጋጀ የኪነ ጉራጌ ላይ የተዘጋጀ የኪነ -ጥበብ መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ የጉራግኛ የፊደል ገበታ ላይ የተዘጋጀ ሰነድ ለታዳሚያን ቀርቦ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት ቋንቋና ስነ-ጥበብ ለማሳደግ ሳይንሳዊ ስልቶችን በተከተለ መልኩ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመለየትና በማጥናት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ገለፁ።

ያለንን ባህልና እሴት መጠበቅና ማሳደግ አንዱ የስልጣኔ መገለጫ በመሆኑ ቋንቋችን እንዳይጠፋና በታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን ሁላችንም የድርሻችንን ወስደን አሁን የተጀመሩ መልካም እንቅስቃሴዎችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ለቋቋችን እድገት ባላቸው እውቀት አቅም የበኩላቸውን እየተወጡ የሚገኙ ሙህራንን በአግባቡ በመጠቀም ትውልድ ባህሉና ማንነቱን እንዲያውቅ ለማስቻል በጋራ ልንረባረብ ይገባል ያሉ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ ባለው አቅም ማህበረሰቡን በማስተባበር የበኩሉን እንደሚወጣም ጠቁመዋል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ እንደተናገሩት ቋንቋችንን ለማሳደግ ሁላችንም የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችንና ማህበራዊ ህይወታቸው ውስጥ በመነጋገር ትውልድ እንዲያውቅ የማስቻል ስራ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የጉራጊኛ ፊደል ገበታ ላይ የተለያዩ የስልጠናና የግንዛቤ ስራዎችን አጠናክረን በመስራት ቋንቋችንን እንዳይጠፋ ሁላችንም በሀላፊነት መስራት መቻል አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ መንዚላት አህመድ እንደተናገሩት እድገትና ለውጥ የሚመጣው የራስን ነገር ከማሳደግ ይጀምራል ያሉ ሲሆን ባህልና ቋንቋችንን ለማሳደግ ከባለፉ ጊዜያ ተምረንና በቁጭት ተነስተን ያገኘናቸው እድሎች መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ከአምና ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው የጉራጊኛ ትምህርት መምህራንን በማሰልጠን ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰው በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች ትምህርቱን እየተሰጠበት ያለበት ሁኔታ ቀርበን በማየት የድርሻው በመውሰድ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሪት ትግስት ይርጋ በበኩላቸው ቋንቋችንና ታሪካች ጠብቀንና አስጠብቀን ማቆየት ግዴታችን በመሆኑ ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ቋንቋ የማንነት መገለጫ በመሆኑ በዚህ ዘርፍ አጋዥ ሊሆኑ የሚገቡ የብሔረሰቡ ተወላጆች በአካባቢያቸው ቋንቋው በመጠቀም ልጆችም እንዲናገሩ በማድረግ ባህላችን ጠብቀን ለትውልድ የሚተላለፍበት ስራ መስራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ቋንቋና ስነ ጥበብ ቡድን መሪ አቶ ባህሩ ሊላጋ እንደተናገሩት

ቋንቋ በተለያዩ ምሁራን ዘንድ በተለያየ መልኩ ቢገለፅም የሰው ልጅ አመለካክቱን፣ እውቀቱን፣ሃዘኑን፣ደስታውን፣ጥበቡን፣ሰልጣኔውን፣ባህሉንና ቋንቋውንም ራሱንም ጨምሮ ለአንዱ የሚያስተላልፍበትና እነዚሁ ከሌላው የሚቀበልበት ነው ብለዋል።

ቋንቋችን እንዳይጠፋ የተጀመሩ ስራዎች ማስቀጠል የሁላችንም ሀላፊነት በመሆኑ ማህበረሰቡ በጉራጊኛ የተፃፉ መፅሐፍ በማንበብ ወላጆች ለልጆች ምሳሌ በመሆን ሀላፊነታቸውን መወጣት መቻል አለባቸው ብለዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ አካላት በሰጡት አስተያየት መንግስት በዚህ ልክ የጉራጊኛ ባህልና ቋንቋ ለማሳደግ እያደረገ ያለው ጥረት አመስግነው ሁላችንም እንደ ባለቤት የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

ትላልቅ የትምህርት ተቋማት ቋንቋውን ለማሳደግ የተለያዩ ጥናቶች ማድረግ መቻል አለባቸው ያሉ ሲሆን በአገኘነው አጋጣሚ ቋንቋችንን በመነጋገር እንዳይጠፋና ለትውልድ እንዲተላለፍ ጥረቶችን ማድረግ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

በመጨረሻም በከተማው ለጉራጊኛ ቋንቋ እና ባህል እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረኩቱ ባለድርሻ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል ።

Previous የኢንተርፕራይዞችን ልማት ለማፋጠንና ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo