በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የአረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀዉ የንግድ ባህል ባዛርና ኤግዚቢሽን የማህበረሰቡ የእርስ በእርስ ትስስሩን የበለጠ የሚያጠናከር ነው:- የወልቂጤ ከተማዉ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ሙራድ ከድር

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የአረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀዉ የንግድ ባህል ባዛርና ኤግዚቢሽን የማህበረሰቡ የእርስ በእርስ ትስስሩን የበለጠ የሚያጠናከር ነው:- የወልቂጤ ከተማዉ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ሙራድ ከድር

ግንቦት 22/2017 ዓ.ም (ወልቂጤ)

በወልቂጤ ከተማ በቀድሞ ተፈራ ሆቴል ግቢ ዉስጥ የንግድና ባህል ባዛርና ኤግዚቢሽን ፌስቲቫል የተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት ተከፈተ።

የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በባዛሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተዉ እንዳሉት ወልቂጤ ከተማ በኢትዮጵያ አንጋፋ ከተሞች ዉስጥ አንዷ ነች።

ከተማዋ እድሜ ጠገብ ስትሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በማሳለጥ፣ የኢኮኖሚ ፖለቲካና ማህበራዊ መስተጋበር በማሳለጥ የድርሻዋን እየተወጣች ይገኛል ብለዋል።

የአረፋ በዓል በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ልዩ ቦታ ተሰጥቶት የሚከበር በዓል ሲሆን በዚህ በዓል የዞኑ ዋና ከተማ የሆነችዉ ወልቂጤ ከተማ ሞቅ ደመቅ ትላለች።

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ዉስጥ የሚገኙ የአካባቢዉ ተወላጆች የእምነቱ ቸከታዮች ዘመዶቻቸዉንና ቤተሰባቸዉ ጥየቃ የሚመጡ እንደሆነም ያመላከቱት ከንቲባዉ ወልቂጤ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ያለባትና ነዋሪዉ ማህበረሰብ እንግዶችን በፍቅር የሚቀበልም እንደሆነም ጠቁመዋል።

ዘንድሮ የሚከበረዉ 1446ኛዉ የኢድ ዓል አድሃ አረፋ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀዉ የንግድ ባህልና ባዛር ኤግዚቢሽን ሻጭና ሸማቹ በአንድ ማዕከል በተመጣጣኝ ዋጋ ጊዜዉን ፣ገንዘቡንና ጉልበቱን ቆጥቦ የሚፈልገዉን የሚሸምትበት እንደሆነም አመላክተዋል።

ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ነጋዴዎች ማህበረሰቡ የሚፈልጋቸዉ የፋብሪካ ምርቶች ይዘዉ የቀረቡ ሲሆን እነዚህም በቅናሽና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ምርቶቻቸዉን አቅርበዋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን አስተዳዳር ልዩ አማካሪ አቶ ዳርጌ ተክሉ እንዳሉት በዞኑ ማህበረሰብ ዘንድ የአረፋና የመስቀል በዓላቶች በድምቀት የሚከበሩና የቱሪዝም መስህብ እንዲሆኑ ታቅዶ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

ሁለቱም ዞኖች በጋራ ያዘጋጁት የንግድ ባህል ባዛርና ኤግዚቢሽን ከግብይት ባሻገር የማህበረሰቡ የእርስ በእርስ ትስስር ይበልጥ የሚያስቀጥል ሲሆን ይህም የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠልም ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን የነጋዴ ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሮዛ አግዛ በበኩላቸዉ ይህ ባዛር ከሌሎች ባዛሮች ለየት የሚያደርገዉ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢድ ዓል አድሃ የአረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ባዛሩም በከተማዉ መዘጋጀቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር አጋዥ እንደሆነም አብራርተዋል።

በመጨረሻም ንግድና ባዛር ኤግሽኑ አስከ 29/09/2017 ድረስ የሚቆይ እንደሆነ አዘጋጅ ኬር ኢቨንትና ፕሮሞሽ የተገለጸ ሲሆን ለዚህ ንግድና ባዛር ኤግዚቢሽን ዝግጅት አስቸዋጽዎ ላበረከቱ አካላት የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርከቶላቸዋል።

በዚህ የንግድ ባህልና ባዛር ኤግዚቢሽን ላይ ከከተማና ከዞን የተዉጣጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የወሊሶ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ተገኝተዋል።

መረጃው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Previous ግንቦት 16/2017 (ወልቂጤ )

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo