
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሀላፊ ኢንጂነር ቶፊቅ ሱልጣን እንደተናገሩት በከተማ አስተዳደር የተጀመረው የመልሶ ማልማት ስራ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው ንቁ ተሳትፎ ከፍተኛ ሲሉ ገልፀዋል።
የወልቂጤ ከተማን መልካም ገፅታ በመገንባት ለኢንቨስትመንት እንዲሁም ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለመፍጠር ከተማ አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀራረብ የሰራ ይገኛል ብለዋል ።
ከዚህ በፊት የነበረውን የከተማዋን ገፅታ የማይመጥኑ ግንባታዎች ከከተማው ነዋሪ ጋር በውይይት ተቀራርቦ በመስራት አሁን ያለንበት አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን።

መንግስት እንደመንግስት ባለው ሀብትና እውቀት በመደገፍ ፣ባለይዞታዎች የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ግንባታ አቅምና ወቅቱን ያማከለ ስራ ለመስራት እንዲሁም የመንግስት ቤቶች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በአክሲዮን በማደራጀት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የተዘጋጀ ዲዛይን በመጠቀም ካልሆነም በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አዘጋጅተው ወደ ልማት የገቡበት አግባብ መኖሩንምን ኢንጅነር ቶፊቅ ተናግረዋል።
የከተማው ነዋሪና ህብረተሰብ ልማቱን በመደገፍ ለጋራ ከተማችን እድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ተቀራርበን ለችግሮቻችን መፍትሄ በማስቀመጥ የተሻለች ለሌላው ምሳሌ የምትሆንና ህዝባችንን የሚመጥን ስራ እንስራ በማለት የከተማ ማዘጋጃ ቤት የሚያደርገው ድጋፍና ክትትል በተሻለ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በከተማ አስተዳደር በመልሶ ማልማት 14 ፕሮጀክቶች ቀርበው ሰባት የሚሆኑ ፕሮጀክቶች በመገምገም ዝግጅት ላይ መሆናቸውን የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅና የመሬት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጃፋር ሻሚል ገልፀዋል።
ማህበረሰብን ለረጅም ጊዜ ከመልሶ ማልማት ጋር ተያይዞ የሚያነሳውን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ለመፍታትና ነዋሪውን የሚመጥን እና የከተማዋን ገፅታ ከፍ በሚያደርጉ መልኩ በመልሶ ማልማት አዋጅና ደንብ መሰረት ስራዎች የተሰሩ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
ማህበረሰቡ ልማቱን አምኖ ተቀብሎ በባለቤትነት የሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ጃፋር ከኢኮኖሚ አንፃር የቀበሌ ቤቶች በአክሲዮን ተደራጅተው እንዲገነቡ በማድረግ በልዩ ትኩረት እየተከናወ ነው ብለዋል።

የግል ይዞታ ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መገንባት የሚችሉትን ወደ ግንባታ በመግባት ለጊዜው የአቅም ውስንነት የገጠማቸውን ማዘጋጃ ቤቱ ከተማውን የሚመጥን ዲዛይን በማዘጋጀት ግንባታ እያከናወኑ መሆናቸው ተናግረዋል።
ማዘጋጃ ቤቱ በመልሶ ማልማት አሰራርና መመሪያ መሰረት ከህዝቡ ጋር በመቀራረብና በመግባባት ተግባራት እየፈተሽን በውጤት ለመስራት ከፍተኛ ጥረት እያደረግን እንገኛለን ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሀላፊ የማስፈፀም አቅም ግንባታና መሰረተ ልማት ሀላፊ ኢንጅነር ፀጋ ፍቅር እንደተናገሩት እንደ ሀገር የተጀመሩ የኢኒሼቲቭ ስራዎች በከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት የተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በከተማው በሚሰራው የ25ኪሎሜትር የኮሪደር ስራ በማስተሳሰር የከተማዋን የማይመጥን ግንባታ በማስወገድ በመልሶ ማልማት የገፅታ ግንባታ ስራ እየተሰራ ነው።
የከተማውን ውበትና ገፅታ ከፍ የሚያደርጉ የመብራት ዝርጋታ፣ የተቀመጠው የህንፃ ቀለም በመቀባት በሚፈለገሙ ልክ ማህበረሰብ ተግባራዊ እያደረገ ነው ያሉ ሲሆን የከተማው ህብረተሰብ የጀመርናቸው የልማት ስራዎች ከግብ ለማድረስ ርብርብ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

በመልሶ ማልማት ስራ ላይ ካገኘናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል አቶ ታምሬ ማሬ ፣ አሸናፊ ቢላል እና መስፍን ቢረዳ በጋራ እንደተናገሩት ለወልቂጤ ከተማ ልማትና መልካም የገፅታ ግንባታ በተቀመጠው ዲዛይን ፈጥኖ ወደ ስራ በመግባት ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።
መንግስት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመፍታት እያደረገ ያለው ድጋፍና ክትትል ከፍተኛ ነው ያሉ ሲሆን የከተማው አመራር ከህዝቡ ጋር በመቀራረብ ልማቱን በቁርጠኝነት የመራበት አግባብ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።
የተጀመሩ የከተማችን ሁሉንተናዊ የልማት የመልካም አስተዳደር ስራዎች ከዳር ለማድረስ የሁላችንም ድጋፍና ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል መቻል አለብን ሲሉ ጠቁመዋል።

