በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ፍትሃዊና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልገሎት ለሁሉም ዜጎች በማድረስ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን እውን እንዲሆን ለማስቻል የሁሉም ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት ገለፀ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በ2015 ዓመተ ምህረት የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የ2016 ዓመተ ምህረት በቀረበው እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በውይይት መድረኩም በከተማ ጤና ፅህፈት ቤት የ2016 ዓመተ ምህረት የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎችም ሪፖርት ቀርቧል።

ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ትርፍን መሰረት የማያደርግ የመድህን አባልነት ሆኖ በአባልነት የሚያቅፋቸው ከመደበኛው ክፍለ ኢኮኖሚ ውጪ ያሉ በአብዛኛው በኢኮኖሚ በማህበራዊ እንቅስቃሴያቸው ከፍተኛ ቁርኝት እና ትውውቅ ያላቸው ህብረተሰብ ክፍሎችን እንደሆነ ከመድረኩ ተገልጿል።

በውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው እንደገለፁት ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ዜጎችን ለጤና አገልግሎት በሚያወጡት ከፍተኛ ወጪ ምክንያት ለከፍ ድህነት እየተዳረጉ ከመሆኑም በላይ አብዛኞቹ የሚከፍሉት ገንዘብ በማጣት ሊድን በሚችል ህመም እየተሰቃዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ እየተጋለጡ በመሆኑ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል ።

ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሁሉም ርብርብ የሚጠይቅ ሲሆን መንግስትም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት በመሆኑ አመራርን በማሳተፍ ፍትሀዊ አሰራሮችን በመከተል ችግሮችን ለይተን ለችግሮቹ መፍትሄ በማግኘት ጤናማ ማህበረሰብ መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካል ሀላፊነት ነው ሲሉ ክቡር ከንቲባው ገልፀዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙባሪክ አህመድ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ፕሮግራም ላይ መልካም አፈፃፀሞችን በማስቀጠል የከተማ አመራር ህዝቡን በአደረጃጀት በማስተባበር መምራትና አፈፃፀምን በመከታተል እየገመገመ እና እየፈተሸ ጉድለቶችን እያረመ መሄድ እንዳለበት አስገንዘበዋል ።

እንዲሁም ቀጣይ የከተማው ማህበረሰብ በቂ መረጃ እንዲያገኝና ተጠቃሚ እንዲሆን በሁሉም ቀበሌዎች እና ጤና ተቋማት ቅንጅታዊ ስራ በመስራት ይህም ተግባር በውጤት የምንገመግም ይሆናል ብለዋል።

በዚህም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ፕሮግራም በምናደርገው ንቅናቄ የወባ በሽታ የመከላከል ስራውም አያይዘን ማስቀጠል መቻል አለበት ሲሉ አቶ ሙባሪክ አህመድ ገልፀዋል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሰለሞን ወርቁ እንደተናገሩት በ2015 ዓመተ ምህረት በማህበረሰብ የጤና መድህን ስርዓት በከተማችን አቅመ የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረገና ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

ቀጣይ የተዘጋጀው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ዘርፍ የ2016 በጀት አመት ዕቅድ ለማሳካት በአዲስ አባላት ምዝገባ እና ነባር አባላት ዕድሳት ወቅት ከታህሳስ 5 እስከ ጥር 30 2016 ዓመተ ምህረት ድረስ የከተማችን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን የማስቻል ስራ ተጠናክሮ ይሰራል ሲሉ አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል ።

እንደ ከተማችን የታቀደው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የ2016 በበጀት ዓመት ዕቅድ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አመራሩንና መላ ህዝቡን በማነቃነቅ አባላትና ቤተሰቦቻቸውን ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉ አካላት ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን [ማዓጤመ] ለከተማው ማህበረሰብ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ እያደረገ ሲሆን ከዚህ የተሻለ ስራ ለመስራት የሁሉም ድጋፍ እና ክትትል አስፈላጊ ነው ሲሉ አንስተዋል።

አያይዘውም አሁን የሚደረገው የአዲስ አባል ምዝገባና እድሳት ህብረተሰቡ ሙሉ መረጃ በመስጠት በከተማ ውስጥ የሚገኙ ቀበሌዎች ለዚህ ስራ መሳካት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

በመጨረሻም በጤና መድህን ንቅናቄ የአባላት ማፍሪያ ስራ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል ።

አንድ_ሆነን_እንስራ_ኢትዮጵያ_ታሸንፍ❗️

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተቀመጡ ሊኮች በመጫን የተቋማችንና ሌሎች የሚዲያ አማራጮችን ይጠቀሙ፡-👇

👉 ዩቲዩብ ፦ https፡//www.youtube.com/@wolkitecityadministrationgov.c/featured

👉 ቴሌግራም፦ https://t.me/WCGCA

👉ኢ_ሜይል፦ www.Woliktecommunication94@gmail.com ይጎብኙ

Previous የጉራጌ ብሔረሰብ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት እና አንፀባራቂ የባህል እሴቶች ካሉት ብሔረሰቦች አንዱ ነው።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo