በግብርና ዘርፍ የሚታየውን መልካም እንቅስቃሴ ቀጣይነት እንዲኖረው የማስቻል ስራ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ፅህፈት ቤት ገለፀ።

በወልቂጤ ከተማ አስተዳድር በጉብርየ ክፍለከተማ በተለያየ የግብርና ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ማህበራት ውጤታማ መሆን እንደቻሉ ገለፁ።የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የግብርና ፅህፈት ቤት ሀላፊ ተወካይና የእንስሳት ጤና ባለሙያ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሱልጣን አክመል እንደገለፁት የግብርና ዘርፍ ትኩረት ሰጥተን ከሰራንበት ውጤታማ የምንሆንበት እና ኢኮኖሚያዊ ለማረጋጋት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የተፈጥሮ ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም በምንችለው አቅማ በተለያዩ የግብርና ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ባለሀብቶችም ሆኑ ማህበራት ማበረታታ እና በመደገፍ ለተሻለ ውጤት በጋራ መስራት ይኖርብናል ሲሉ አቶ ሱልጣን ገልፀዋል።በከተማችን በጓሮ አትክልት ፣በከብትና በዶሮ ሀብት እንዲሁም በሰብል ልማት የተሰማሩ ወጣቶች የተሻለ መልካም የስራ እንቅስቃሴ በማድረግ ለሌሎችም በማነሳሳት እና የስራ እድል መፍጠር መቻሉንም ተናግረዋል።

በጉብርየ ክፍለከተማ አባፍሯንሷ ማርቆስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በጓሮ አትክልት የተሰማሩ ወጣቶች መኖራቸውን ጠቅሰው በዞን ግብርና መምሪያ የጄኔሬተር ድጋፍ ከመጌቻ ወንዝ መስኖ በመጥለፍ የሚበረታታና የሚደገፍ ስራ እየሰሩ ያሉ ወጣቶች መኖራቸውን አቶ ሱልጣን አንስተዋል።እንዲሁም በግለብ ደረጃ ባላቸው ቦታ የተለያየ የግብርና ዘርፍ ምርት ላይ ተሠማርተው ለህብረተሰቡ ምርት ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ያሉ ማህበራት መኖራቸውንም ጠቅሰዋል ።እንዲሁም የገበያ ትስስር በመፍጠር ምርቶች ቀጥታ ከህብረተሰቡ ጋር በማገናኘት አምራቹምና ሸማቹን የማቀራረብ ስራ በትኩረት እየሠራን ነው ሲሉ አቶ ሱልጣን ተናግረዋል።አያይዘውም የግብርና ዘርፍ ለመሰማራት በርካታ ማህበራት የተደራጁ መኖራቸውን ጠቅሰው የተለያየ የግብዓትና የቦታ የማመቻቸት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል ።አክለውም የዋቤን ወንዝ ሀብታችንን በመጠቀም ማህበራት እና አቅም ያላቸው ባለሀብቶች በመስኖ ስራ ላይ እንዲሰማሩ የከተማ ግብርና ትኩረት ሰጥቶ እየሠራበት እንደሚገኝም አቶ ሱልጣን አብራርተዋል ።ተጠቃሚ ከሆኑ ካነጋገርናቸው ወጣቶች መካከል በተሰማሩበት የግብርና ዘርፍ ዉጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል ።ከተማ ግብርና እያደረገ ያለው እገዛና ክትትል ከፍተኛ ሲሆን የተሻለ ስራ ለመስራትና ምርቶቹ ለሸማት እንዲቀርብ የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸውም ጠይቀዋል ።እንዲሁም በበቂ ሁኔታ የግብዓት አቅርቦት ችግር መኖሩን አንስተው እንዲሁም በከተማችን የመኖ አቅራቢ ማህበራት አለመኖር ለስራቸው እንቅፍት እንደሆነባቸው ተናግረዋል።

Previous የመስቀል በአልን አስመልክቶ ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የተላለፈ መልዕክት ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo