የመስቀል በአልን አስመልክቶ ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የተላለፈ መልዕክት ።

መስከረም 13/2016 ዓ.ም (ወልቂጤ)

በጉራጌ ዞን ርዕሰ መዲና በሆነችው ወልቂጤ ከተማ የመስቀል በዓልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን በሰላም አክበረው እንዲመለሱ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት መደረጉን በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

በጉራጌ ብሔር ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት መካከል የመስቀል በዓል አንዱ ሲሆን ይህን በዓል ለመታደም ወደ ወልቂጤ ከተማ የሚመጡ እንግዶች ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብሩ ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላትንና ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት ለመስራት ቅደመ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል ።

ወደ ዞኑ ማዕከል በሆነችው ወልቂጤ ከተማ ባዓሉን ለማክበር ብዙ ቁጥር ያላቸው የዞኑ ተዋላጅና ወደ አጎራባች አካባቢዎች የሚጓዙ እንግዶች ሰላማዊ የሆነ የትራፊክ ፍስት እንዲኖር ከትራፈክ ፖሊስና በጎፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

የመስቀል በዓልን አስመልክቶ የከተማው የንግዱን ማህበረሰብ በማሳተፋ የንግድ ትሪትና ባዘር በከተማው እየተካሄደ በመሆኑ ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸውን የፍጆታ እቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እንዲችል እድል መፈጠሩን የተናገሩት አቶ እንዳለ ስጦታው በዚህም የኢንቨስትመንት ፍሰት ለመጨመር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል ።

የሚመጡ እንግዶችም የባህላቸው መገለጫ የሆኑትን እቃዎች በመግዛት ለሌሎች አከባቢዎች ማስተዋወቅ እንዳለባቸውና ከዞኑ ውጪ የሚኖሩ ተወላጅ ባለ ሀብቶችና ማህበረሰቡ ለከተማው እድገትና ልማት እያደረኩት ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ማጠናከር እንዳለባቸው አቶ እንዳለ ስጦታው ገልጸዋል ።

በዓል ለማክበር የሚመጡ እንግዶች በሰላም ገብተው በሰላም እንዲመለሱ የከተማው ማህበረሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የሰላም አምባሳደርነቱን ማሳየት እንዳለበት የገለጹት ከንቲባው እንዲሁም በሀይማኖት፣ በብሔር እና ሌሎች ህብረተሰቡን ለማጋጨትና ልማት እንዳይሰፍን የሚንቀሳቀሱ አካላትን ሴራ መላው ህብረተሰብ ተረባርቦ ማክሸፍ ይኖርበታል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ለኢንቨስትመንት ልማት ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠረ መሆኑን የሚጠቁሙት አቶ እንዳለ ስጦታው ባለሀብቶች በተለይም የዞኑ ተወላጅ ኢንቨስተሮች በከተማዋ እንዲያለሙና እንዲጠቀሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

እንዲሁም በዓሉን ድጋፍ ከሚሹ ወገኖች ጋር ለማክበር ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑንና ማህበረሰቡም ያለውን ከሌላው ጋር በእኩል ተካፍሎ መብላት የሚችልበትና መተሳሰብን የሚፈጥሩበት በዓል እንዲሆን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ለእምነቱ ተከታዮች በድጋሚ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ።

አንድ_ሆነን_እንስራ_ኢትዮጵያ_ታሸንፍ❗️

May be an image of 1 person, suit, newsroom and text
Previous የከተማውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው አስታወቁ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo