የጉራጌ የመተባበር፣ የመተጋገዝን ጠንክሮ የመስራት እሴቶች ተጠብቀው እንዲቆዩና ወደ ተተኪው ትውልድ ለማሸጋገር የጉራጌ ሸንጎ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ሸንጎው እንዲጠናከር በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው

ህዳር 28/2017(ወልቂጤ)

የጉራጌ አንድነትና ልማት ለማጠናከር ምሁራን አመራሮችና ባለሀብቶች ተሳትፏቸው ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለፁ።

የጉራጌ አማካሪ ምክርቤት ከፌደራል፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልና ከአዲስ አበባ የብሄሩ ተወላጅ አመራሮች፣ ከጉራጌ ዞኖች፣ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም ከባለሀብቶች፣ ከአርቲስቶች፣ ከሀይማኖት አባቶች ጋር “ተግባቦታችንና አንድነታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ተወያየ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት የጉራጌ አንድነትና ልማት ለማጠናከር የተጀመሩ ስራዎች ማጠናከር ይገባል።

በተለይም የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ህብረተሰቡን የሚመጥን ስራ በመስራት የማህበረሰቡን አንድነትና ልማት ማጠናከር እንዲችል ባለሀብቶች፣ ሙህራን፣ አመራሩና መላው የጉራጌ ዞኖች ማህበረሰብ የሚያደርጉት ድጋፍ ማጠናከር እንዳለባቸው ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል።

የጉራጌ የመተባበር፣ የመተጋገዝን ጠንክሮ የመስራት እሴቶች ተጠብቀው እንዲቆዩና ወደ ተተኪው ትውልድ ለማሸጋገር የጉራጌ ሸንጎ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ሸንጎው እንዲጠናከር በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል።

አክለውም ርዕሰ መስተዳድሩ የብሄሩ ተወላጅ ባለሀብቶች በመላው ሀገሪቱ ከሚያደርጉት ልማት ጎን ለጎን በሁለቱም ዞኖች መዋዕለንዋያቸውን በማፍሰስ ህብረተሰቡ በልማት ለማስተሳሰር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በዞኑ በሁሉም ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች ሲሆኑ ዞኑ ያሉትን ፀጋዎች አሟጦ በመጠቀም የማህበረሰቡ የልማት ጥያቄዎች መመለስ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት የብሄሩ ባህል፣ ታሪክና ስነ ልቦና የሚመጥን የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ለማዘጋጀት ቅድመዝግጅት እየተደረገ መሆኑ አቶ ላጫ ገልጸዋል።

የጉራጌ አንድነትና ልማት ለማፋጠን የጉራጌ ልማትና ባህል አቅም ማጎልበት እንደሚገባ የተናገሩት አቶ ላጫ ልማት ማህበሩ በተለያዩ ቦታዎች የጀመራቸው ስራዎች ለማጠናቀቅ ሁሉም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አመላክተዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በበኩላቸው ዞኖቹ በልማት ለማስተሳሰር እና የብሄሩ ተወላጆች ግንኙነት ለማጠናከር የውይይት መድረኮች ሊዘጋጁ ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ባህልና ቋንቋ ለማሳደግ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ፣ የሁለቱ ዞኖች ባህልና ቱሪዝም መምሪያዎች ከልማት ማህበሩ ጋር በመቀናጀት መስራት እንዳለባቸው አቶ ሙስጠፋ ገልጸዋል።

የጉራጌ ባህልና ልማት ማህበር እና የጉራጌ ህዝብ አማካሪ ምክርቤት የተግባር አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የአመራሩ አንድነትና ጥንካሬ ሰላም ለማስፈን፣ አንድነት ለመፍጠርና ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ የሁለቱ ጉራጌ ዞኖች አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

በዚህም አመራሮቹ ልምዳቸው፣ እውቀታቸውና ክህሎታቸውን በመጠቀም ህዝባቸውን ለማገልገል በቁርጠኝነት መሰራት ይጠበቅባቸዋል።

የህዝቡ አንድነትና ትስስር በማጠናከር በልማት ስራዎች በንቃት እንዲሳተፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

Previous እኔና መሬቴ አብረን እንኑር ከሚል አሰተሳሰብ በመውጣት ከተማዋ በማልማት ጉዳይ ላይ የጋራ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo