የወልቂጤ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስትየውሃ፣ መስኖናማዕድንልማት ቢሮ አስታወቀ።

ግንቦት 6/2016 ዓ.ም/ወልቂጤ

የከተማው ዉሃ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የተቋቋው የኢመርጀንሲ ቦርድ አባላት እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል ።

የማዕከላዊኢትዮጵያክልል ውሃ፣መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዴዊት ኃይሉ በመደረኩ ላይ እንደገለጹት የወልቂጤከተማ የንፁህ የንጹህ ዉሃ አቅርቦት ለማሻሻል የተቋቋመው የኢመርጀንሲ ቦርዱ ባስቀመጠው የድርጊት መረሀ ግብር መሠረት በንኡስ ኮሚቴዎቾ የተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት ቀርበው የጋራ ውይይት ተደርጓባቸዋል ብለዋል ።

የወልቂጤ ከተማ የዉሃ አገልግሎት ተቋም አቅም ከማጎልበት፣ ከህገወጥ ቅጥያ፣ከመስመር ብልሽት፣ ከፍትሃዊ የዉሃ ስርጭት ሌሎች በቀጣይ የከተማዉ ዉሃ አቅርቦት በዘላቂነት ለማሻሻ የተጀመሩ ተግባራት በዝርዝር ተገምግሟል።

በተለይ የኢመርንጀንሲ ወደ ተግባር ከገባ አጭር ጊዚ ቢሆንም በተጀማመሩ ተግባራት ተስፋሰጪ በመሆናቸው በቀጣይ በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመረው ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ የወልቂጤ ከተማ የዉሃ አቅርቦት ለማሻሻል የውሃ አገልግሎት በአዲስ ሪፎርም ለማድረግ ከስራስኪጅ ጀምሮ የማኔጅመንት አካላት በቴክኒካል እውቀትና ሰነመግባር የተሻሉ እንዲሆኑ ወቅቱንና የከተማው አሁናዊ እድገት የሚመጥን ለማድረግ በኢመረጀንሲ ቦርዱና በመደኛ ቦርድ አየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች በመሆናቸው በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

ከመብራት ኃይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ችግር ለመቀነስ ከፌደራል ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጣ ጀነሬተር ለመጠቀም የቦታ መረጣ ስራ መከናወኑን ጠቅሰው የተከላና የማገናኘት ስራ በሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ይከናወናል ብለዋል ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትል እና የመጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊና የኢመርጀንሲ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ሳሊም ባርጊቾ ቢሮው የከተማው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጅት ሰፊ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በኢመርጀንሲ ቦርድ ስር የተቋቋሙ ሁሉም ንኡስ ኮሚቴ ባቀዱት እቅድ መሠረት ወደ ተግባር መግባታቸውንና እሰካሁን በኢመርጀንሲ ቦርዱ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በዝር አቅርበዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው በበኩላቸው እንደ ከተማ አሰተዳደር የገጠመን የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት አሁን ላይ ከየተኛውም ተግባር ቅድሚያ ተሠጥቶ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ።

የዉሃ አገልግሎት ተቋም በተሻ ሰው ኃይል ለማደራጀት የሪፎርም ስራው ከፐብሊክ ስርቪስና ከሌሎች ተቋማት በተውጣጣ ኮሚቴ አየተመራ ነው ብለዋል።

የውሃ ስርጭቱ ፈትሃዊ እንዲሆን፣ ህገወጥ ቅጥያዎች ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ህጋዊ የማድረግና የአገልግሎት ክፍያውን አሟጦ ለማሰባሰብ በተደረገው ጥረት አበራታች ውጤት ተመዝግበዋል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ የውሃ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወንዴ አምዴ ተቋሙን ለማዘመንና ባለሙያዎች አቅም የማጎልበት ስራ አየተሰራ ነው ብለዋል ።

የዉሃ ስርጭቱ ፍትሃዊ እንዲሆንና በሁሉም መሰመሮች የሚስተዋሉ የብልሸትትና መጠን የመቀነስ ስራ እየተሠራ በመሠራቱ ወደ ዋና ታንከር የሚገባው ውሃ መጠን መጨመሩን አብራርተዋል ።

በቀጣይ በከተማው አሰተዳደርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተጀመረው ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትየሪፎርም ስራው በጥናት ላይ የተመሠረተናበቀጣይበከተማውተጨባጭ ለውጥ ማምጣት በሚችል መልኩ ሊሰረራ እንደሚገባም አሰተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል ።

የሚመረተው የውሃ አቅም ለማሳደግ በሁሉም መስመሮች የተጀሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብሐዋል።

ሁሉም የቦርድ አባላት በቀጣይ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በመናገር የእለቱ መድረክ ተጠናቋል::

Previous ሚያዝያ 27/2O16 ዓ/ም [ወልቂጤ]

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo