የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ!!
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በጉብሬ ክፍለ ከተማ ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቦታ ለአልሚዎች በመደበኛ ጨረታ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከቀን 28/O8/2O16 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለ1O [አስር] ተከታታይ የስራ ቀናቶች በከተማው ዋና ማዘጋጃ ቤት እና በጉብሬ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን ማዘጋጃ ቤቱ ይገልፃል።
የማህበረሰቡ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ታስቦ የተዘጋጁት ቦታዎቹ የመሰረተ ልማት ችግር የሌለባቸውና ለመኖሪያ ምቹ መሆናቸው ለመግለፅ እንወዳለን።
በተጨማሪም ቦታዎቹ በአካል ሄዶ ማየት ሚፈልግ ሰው ዘውትር በስራ ሰአት ወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።
አጠቃላይ የጨረታው ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች ተገልጿል።
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ 721/2OO4 መሰረት የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ
ክፍል አንድ፡- የጨረታ መመሪያ
1. ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተቀመጠውን የጨረታ መመሪያ መሰረት መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ከመመሪያው ውጭ የቀረቡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
1.1.1. ኦሪጂናል እና የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት ሰነድ ብቻ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ የመስሪያ ቤቱ ክብ ማህተም ያላረፈበት ኦሪጂናል ያልሆነ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
1.1.2. አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም፡፡
1.1.3. ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማስገቢያ እና የሀሳብ ማቅረቢያ ላይ የተመለከቱትን በጥንቃቄ እና በግልጽ ሊነበብ በሚችል መልኩ ማስፈር ይኖርበታል።
1.1.4. በግልጽ የማይነበቡ ስርዝ ድልዝ የበዛባቸው ሰነዶች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡
1.1.5. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረትበትን የቦታ ዋጋ በፊደል እና በአሃዝ መሞላት አለበት፡፡ በፊደል እና በአሃዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ተቀባይነት አለው፡፡
1.1.6. ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ በመንተራስ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
1.1.7. በጨረታው የሚሳተፈው አካል [ድርጅት ወይም ማህበር] ከሆነ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱ ማህተም በሰነዶቹ ሁሉም ገፅ ላይ ማኖር ይኖርበታል፡፡
1.1.8. ተጫራች የዋጋ እና የሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዶቹን በአግባቡ በመሙላት እና በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የተጫራች ስም እና የቦታው ልዩ ፕሎትና የፕሎት ቁጥር በግልጽ በመፃፍ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውሰጥ ማሰገባት ይኖረባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ማንኛም ሰነድ ዋጋ አይኖረዉውም፡፡
1.1.9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ የተጫረተበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከአምስት በመቶ ያላነሰ በማዘጋጃ ቤቱ ስም በማስገባት ከዋጋ እና የሀሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
1.1.1O. የሚቀርበው የቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የጨረታ ዋጋ ለንግድ ከ2O በመቶ እና ለመኖርያ ከ1O በመቶ ማነሰ የለበትም፡፡
1.1.11. ማዘጋጃ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
1.2. ከጨረታ ውጪ የሚያስደርጉ ድርጊቶች
1.2.1. የተጭበረበረ ወይም ከሚፈለገው በታች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ያቀረበ ተጫራች፣
1.2.2. የተጭበረበረ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ እና የውክልና ማስረጃ ሰነድ ያቀረበ ተጫራች፣
1.2.3. በአዋጁ መሰረት በከተማው በወጡ ጨረታዎች አሸንፎ ውል ሣይፈጽም ቀርቶ ገደብና ቅጣት የተጣለበት የጊዜ ገደብ ያልተጠናቀቀ ተጫራች ከሆነ፤
1.2.4. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ያስገባ ወይም በጨረታ ዋጋ ላይ ከሌሎች ተጫራቾች ጋር የተመሳጠረ ከሆነ፣
1.2.5. ተጫራቹ ቀደም ሲል በወሰደው መሬት ላይ ከ5O% በታች ሳያጠናቅቅ ሁለት ጊዜ የመሬት የመጠቀም መብቱን ያስተላለፈ መሆኑንና ግንባታ ባለማጠናቀቁ መሬት ተነጥቆ የተወሰነበት የቅጣት ዘመን ያልተጠናቀቀ ከሆነ፣
1.2.6. የጨረታውን ሂደት የሚጻረሩ ወይም የሚያዛቡ ድርጊቶች የተፈጸመ ሲሆን፣
1.3. የጨረታ ማወዳደሪያ መስፈርት እና ሌሎች ማብራሪያዎች
1.3.1. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የሊዝ ጨረታ ዋጋ ከመቶ ሰማንያ [8O%] ነጥብ ሲኖረው፣ የቅድመ ክፍያ መጠን ከመቶ አስራ ሁለት [12%] እና ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ ከመቶ ስምንት [8%] ይኖረዋል፡፡ የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሦስቱ ነጥቦች ድምር በሚገኘው ውጤት ነው፡፡
1.3.2. ሁለት እና ከዚያ በላይ ተጫራቾች በሶስቱም መወዳደርያ መስፈርቶች እኩል ያመጡ ከሆነ ባቀረቡት የህንፃ ከፍታ የሚለዩ ሲሆን በሁሉም መስፈርቶች እኩል ከሆኑ ግን አሸናፊው በዕጣ ይለያል፡፡ በሁሉም መስፈርቶች እኩል ወጥተው ሴት ብቸኛ ተወዳዳሪ ካለች ቅድሚያ ይሰጣታል፡፡
1.3.3. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለጸለት በአስር የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን ቅድመ ክፍያ በመክፈል የሊዝ ውል ይፈጽማል፡፡ በተጠቀሰው ቀን እና በተጨማሪ በማስጠንቀቂያ በሚሰጠው ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ይደረጋል።
ሁለተኛ እና ሶስተኛ የወጡት ተጫራቾች አንደኛ በወጣው ዋጋ ለመውሰድ ከፈለጉ እንደየ ቅደም ተከተላቸው ይሰጣቸዋል፡፡
ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ዋጋ እና ሀሳብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
1.3.4. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቀን ከ28/O8/2O16 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለ1O ተከታታይ የስራ ቀናቶች ሲሆን በ O9/O9/2O16 ዓመተ ምህረት እስከ ቀኑ 6፡OO [ዘጠኝ ሰዓት] ሰአት የጨረታ ሰነድ የሚሸጥ ሲሆን ከ ቀኑ 9፡3O እስከ 11፡OO [አስራ አንድ ሰዓት] የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ሆኖ የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው በዛው ዕለት ከቀኑ11፡3O [አስራአንድ ሰዓት ተኩል] ሲሆን ጨረታው በማግስቱ 12/O9/2O16 ዓመተ ምህረት ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡OO [ሶስት ሰዓት] በወልቂጤ ከተማ ምክር ቤት አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
1.3.5. ተጫራቾች ቦታው በአካል መመልከት ከፈለጉ ከጨረታ አስፈፃሚ ቡድን ጋር በመሆን በO6/O9/2O16 ዓመተ ምህረት ከጠዋቱ 3፡OO መጎብኝት ይችላሉ፡፡ ከዚህ ውጪ ባለው ጊዜ በፕላን መመልከት ይቻላል፡፡
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽህፈት ቤት።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተቀመጡ ሊኮች በመጫን የተቋማችንና ሌሎች የሚዲያ አማራጮችን ይጠቀሙ፡-![]()
ዌብሳይት፦ https://www.wolkitecityadministration.gov.et
ዩቲዩብ ፦ https፡//www.youtube.com/@wolkitecityadministrationgov.c/featured
ቴሌግራም፦ https://t.me/WCGCA
ኢ_ሜይል፦ከ www.Woliktecommunication94@gmail.com ይጎብኙ![]()
ስልክ፦ +251113659879

