የካቲት 20/2016ዓ.ም[ወልቂጤ]
የታቀዱ እቅዶችን ለማሳካት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከርና የባለድርሻ አካላትን ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለፀ።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ጽህፈት ቤት የ1ኛ ግማሽ አመት በዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።
በመድረኩም የሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የእቅድ የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ከከተማው አመራርና ከሴክተር መስሪያ ቤት ማኔጅመንት አካላት ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው እንደገለፁት በማህበራዊና በኢኮኖሚው ዘርፍ ተግባርን ለማሳካት ተግዳሮት የሆኑትን ነገሮች በመለየት ጥንካሬውን በማስቀጠል ጉድለትን ማረም የተሻሉ ሥራዎችን እንደሚያስፈልግ ገልፀው።

የሚነሱ የመልካም አስተዳድር ችግሮች በየደረጃዎ ህዝቡ የሚያነሳዉ የልማት ጥያቄዎች በበጀት አስደግፎ መመለስ ግድ የሚል እንደሆነም አመላክተዋል።
ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተጋገዝና በመናበብ ህዝብን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ የሚያስችል ተግባር መፈጸም ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመድረኩ የተነሱ ሃሳቦችን ለቅሞ በመያዝ ለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫና የእቅድ አካል ተደርጎ ሊሰራበት ይገባልም ብለዋል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተካልኝ አቡሌ እንደገለፁት ምን ታቅዶ ምን ተሰራ ብሎ መጠየቅ የተቋማችን ትልቁ ጉዳይ በመሆኑ እያንዳንዱ የሚታቀዱ እቅዶች እስታንዳርድን መሠረት ያደረገ መሆን መቻለ አለባቸው።

የህዝብ ተጠቃሚነት በተገቢዉ ለማረጋገጥና በዘርፉ ዉጤታማ ስራ ለመስራት የመረጃ ጥራትና ወቅታዊነት ላይ ትኩረት አድርጎ መሰራት አለበት ያሉ ሲሆን።
በአንዳንድ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ፈጣንና ጥራት ያለው መረጃ ከማድረስ ጋር የሚታዩ ውስንነቶች በተገቢዉ በመቅረፍ በዘርፉ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባም አቶ ተካልኝ አቡሌ አመላክተዋል።
ከተሳታፊዎች ከተነሱ ሀሳቦች መካከል ለወጣት ስራ ዕድል ከመፍጠረ፣የከተማ ግብርናን ከማዘመን፣የሴቶችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ፣የትራንስፖርት ስርአቱን በተመለከተ፣ጤና፣ትምህርት፣ከገቢና ከደረሰኝ ስርአት፣ከተማዋን መልሶ ከማልማትና ለሸማቾች የሚቀርቡ ግብአቶች ቁጥር ከማህበረሰቡ ጋር የተመጣጠነ አለመሆን እና መሠል ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው።

ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከመድረክ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ያልተከናወኑ ተግባራት ለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫና የእቅድ አካል ተደርጎ ሊሰራበት እንደሚገባም ከመድረኩ ተመልክቷል ።


