የካቲት 18/2016 ዓ.ም
የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ አዳዲስ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎችን በማስፋትና በማጠናከር ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ስራዎች ላይ በትኩረት ይሰራል።
የበጀት እጥረት የሚቀርፉና ሀብት የሚያስገኙ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ያሉት አቶ ደምስ ገብሬ በዚህም ከባድ፣ቀላልና መለስተኛ የሀርድ ዌር፣ በሶፍት ዌር፣ጥገና ላይ በተሰራው ስራ 1ሚሊየን 3መቶ 5ሺህ 500 ብር ከመንግስት ይወጣ የነበረ ገንዘብ ማዳን መቻሉ አስታውቀዋል።
አያይዘውም ተቋማት የቪድዮ ኮንፈረንስና በዙም ሚቲንግ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተሰራ ሲሆን በዚህም 3መቶ 43 ሺ 950 ብር ማዳን መቻሉ አመላክተዋል።
አቶ ደምስ አክለውም የሲስተም ልማት ስራ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ አሰራሮችን መዘርጋት፣ስራዎችን ማቅለልና ወጪን በማዳን ገቢ ማስገኘት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የተጀማመሩ በኦን ላይን ንግድ ዘርፍ የሚሰሩ የብቃት ማረጋገጫ ቴክኖሎጂዎች ማብቃት መደገፍና ቀጣይነት እንዲኖራቸው መስራት ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ደምስ ተናግረዋል።

አሁን አሁን ዞኑ የሚታወቅበት ያለው አዳዲስ የተጀማመሩ የፈጠራ ስራዎችን በማብቃት፣በመደገፍና በማሸጋገር ህብረተሰቡና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ውጤታማ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ አስገንዘበዋል።
በተለይም በግል የሚሰሩ የፈጠራ ሰዎችን ልዩ ትኩረት መስጠትና በትምህርት ቤተች ያሉ ክበባቶችን ማጠናከር እንደማገባ አስረድተዋል።
ከፌደራልና ከክልል የሚወጡ አዳዲስ ሲስተሞችን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ውስንነት ያለ ሲሆን አዳዲስ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎችን በማጠናከር ቀልጣፋ፣ፈጣንና ወቅቱን የሚዋጁ የቴክኖሎጂ ስራዎችን ለማስፋት ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

ዞኑ እስካሁን በሰራቸው ስራዎች በክልል ደረጃ ጥሩ አፈጻጸም እንዳለው አስታውቀው ቀጣይ በዘርፉ የተጀማመሩ ስራዎችን በማጠናከርና ችግሮችን በመለየት ወቅቱን የሚመጥኑ የቴክኖሎጂ የኢኖቬሽን ስራዎች እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንደተናገሩት በየ ተቋሟት የተበላሹ ከባድ፣ቀላልና መለስተኛ የሀርድ ዌር፣በሶፍት ዌር፣ጥገና ላይ ሰፋፊ ስራዎች እየሰሩ እንደነበር አንስተዋል።

በቀጣይም በግማሽ አመቱ ያልተከናወኑ ስራዎችን በመለየት የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎች አጠናክረን እንሰራለን ብለዋል።

በመድረኩም የመምሪያው ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬና የማኔጅመንት አካላት፣ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር የመጡ የጽ/ቤቱ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣የምስራቅ ጉራጌና የየም ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በመጨረሻም በአመቱ ጥሩ አፈጻጸም ያመጡ መዋቅሮች እውቅናና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን መድረኩ ሌሎች ስልጠናዎችን ለመስጠት 2 ቀን የሚቆይ እንደሆነ ታውቋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።




