የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ከትምህርት ጽህፈት ቤት በመተባበር “የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሁለንተናዊ ብልጽግና ” በሚል በትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ለሳይንስ ክበባት ተጠሪዎች ናየፈጠራ ባለቤቶች ስልጠና ተሰጠ።

የካቲተት 1/2017ዓ.ም(ወልቂጤ )

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ከትምህርት ጽህፈት ቤት በመተባበር “የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሁለንተናዊ ብልጽግና ” በሚል በትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ለሳይንስ ክበባት ተጠሪዎች ናየፈጠራ ባለቤቶች ስልጠና ተሰጠ።

በእለቱም በሳይንስ ና ቴክኖሎጂ ሳምንት አከባበርና የ አከባበሩ ሂደት መርሀግብር ዙሪያ እንዲሁም በአእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ ዙሪያ ምክክር ተደርጓል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀምዱ ካሚል እንደገለጹት በ2025 ኢትዮጵያ ከወረቀት ነጻ አገልግሎት ዲጂታላይዜሽን ለማስፋፋት የታቀደው እቅድ ለማሳካት በትምህርት ቤቶች የሚገኙ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባት መነሻ ስለሚሆን ክበባትአደረጃጀት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።

አሁን አለም ያለችበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ሀገራችን ለማቀላቀል በየትምህርት ቤቶች የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎች ን እውቅና መስጠት ና ማበረታታት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል ።

የትምህርት ጽህፈት ቤት ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ መለሰች እንደገለጹት ከከተማችን አልፎ በዞኑ በርካታ በፈጠራው ዘርፍ አቅም ያላቸው ተማሪዎችና መምህራን ስላሉ ከጎናቸው ሆነን ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንሆኑ ማገዝ ይጠበቅብናል ብለዋል።

አያይዘውም ለፈጠራ ስራው ውጤታማነትም ከርዕሳነ መምህራን ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ ተጠሪዎች የድርሻውን በመገዝ ለውጤት መብቃት እንደሚገባ አሳስበዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡን ተሳታፊዎች በበኩላቸው በየትምህርት ቤቶች ለሚገኙ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባትን በዚህ ልክ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱ ይበል የሚያስብል መሆኑን አንስተዋል ።

ከተማዋን ከአቻ ከተሞች አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጉና ውጤታማነታቸው የተመዘኑ ና ከተማዋን የሚያስጠሩ የፈጠራ ስራ ባለቤቶችን ከተማ አስተዳደሩ በሀሳብም በገንዘብም ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

ከመድረኩ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊ በፈጠራ ስራ ና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ከመድረኩ ከተሳታፊዎች ለተነሱ የግልጸኝነት ና ሌሎች በፈጠራው ስራው ዘርፍ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ።

Previous እናቶች በወሊድ ወቅት የሚገጥማቸው ህመምና ሞት ለመቀነስ ባለድርሻ አካት የሚያደርጉት ቅንጅታዊ አሰራር ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo