የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ480 የህግ ታራሚዎች የይቅርታ ማድረጉን ተከትሎ በወልቂጤ ማረሚያ ተቋም የሚገኙ 86 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ መለለቃቸውን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ሃላፊ አቶ ኤልያስ ሰብለጋ ገለፁ።

ሚያዚያ 1 /12018 ዓ.ም ወልቂጤ

የዘንድሮዉን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግስት ለ480 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድርጉ ተከትሎ በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም 86 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ ተለቀዋል።

የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤልያስ ሰብለጋ እንዳሉት የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ480 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተከትሎ የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም 86 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ ለቋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው 86 ታራሚዎች መካከል 83ቱ በሙሉ ይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነ ሲሆን፥ 3ቱ ከእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ቅናሽ በማድረግ ወደ 25 ዓመት ዝቅ መደረጉን አስረድተዋል።

ታራሚዎች በቆይታቸው ጸባያቸው ጥሩ በመሆኑ ፣ ከተበዳይ ቤተሰብ ጋር እርቅ መፈጸማቸውና ስነ ምግባራቸው የተስተካከለ በመሆኑ ይህንን ይቅርታ ሊያገኙ የቻሉ መሆኑም አመላክተው እነዚህም ከማረሚያው ከወጡ በኃላ የትኛውም ወንጀል መፈጸም እንደሌለባቸውም ተናግረዋል።

በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ታራሚዎች የህግ ትምህርት ግንዛቤ የሚሰጣቸውና ሰበአዊ መብታቸው እንዳይጣስ ይደረጋል እንዲሁም መደበኛ ትምህርት ይሰጣቸዋል ያሉት አቶ ኤልያስ የተለያዩ አካላትን በማስተባበር በማረሚያ ቤቱ ውሰጥ የተደራጀ ቤተ መጽሐፍት ያለ ሲሆን ታራሚዎችም በስፋት የንባብ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውም

የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ሀላፊ ኮማንደር ታምሬ ደንድር እንዳሉት በዛሬው እለት የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ በተቋሚ ከሚገኙ ታራሚዎች መካከል የዞኑ መልማይ ኮሚቴ ወደ ይቅርታ ቦርድ ከተላኩት ታራሚዎች ውስጥ 86 ታራሚዎች በርዕሰ መስተዳደሩ ተቀባይነት አግኝቶ የይቅርታ ተጠቃሚ ሆነዋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች ውስጥ 3 ታራሚዎች ከእድሜ ልክ ወደ 25 ዓመት ዝቅ የተደረገላቸው ታራሚዎች ሲሆኑ 83 ታራሚዎች በዛሬው እለት ከእስር እንዲወጡ ተደርጓል ብለዋል።

ታራሚዎች በቆይታቸው በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው ይሰሩ የነበረና ከማህበረሰቡ ጋር ሲቀላቀሉ የወንጀል አስከፊነት ላይ ግንዛቤ በመፍጠርና በቆይታቸው ባገኙት ሙያ ላይ ተሰማርተው መስራት ይነርባቸዋል ብለዋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል የህግ ታራሚ አቶ ሳዳም ሳኒ ፣ አቶ ፋንታሁን ወንድሙ ፣ እንዲሁም ሰላም ከድር እንዳሉት በአሉን ምክንያት በማድረግ ከእስር መለቀቃቸው በጣም ደስተኛ እንደሆኑና ከወጡ በኃላም ስለ ወንጀል አስከፊነት ለህዝቡ የማስማር ስራ እንደሚሰሩም አስረድተዋል።

የወንጀል አስከፊነት የሚታወቀው ማረሚያ ቤት ሲገባ እንደሆነም ያመላከቱት ታራሚዎቹ እስር በእኛ ይብቃ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።

Previous የመደመር መንግስት እሳቤዎችን እውን ለማድረግና የከተማችን ህዝብ የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን ክትመትና ኢንዱስትሪን ማስፋፋት ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራን ነው፦ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo