የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የህብረት ስራ ማህበራት ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ተገለፀ።

20/2016ዓ.ም [ወልቂጤ]

የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የህብረት ስራ ማህበራት ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ተገለፀ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ንግድ ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት የህብረት ስራ ማህበራት አመራርና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት አደረገ።

በውይይት መድረኩም የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የከተማ ንግድ ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ሀሊማ ዲጋ እንደገለፁት ህብረት ስራ ማህበራት ለትርፍ ያልተቋቋሙ ህዝብን የሚያገለግሉ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

ከህብረተሰቡ ካላቸው ቅርበት እንዲሁም ካፒታልና አቅም ኑሮ የማረጋጋት ስራ ላይ የድርሻቸውን በመወጣት የተለያዩ የፋብሪካ ፣የግብርና ውጤቶች የሚያቀርቡ በመሆናቸው ከአምራቾችና ከአርሶ አደሩ ቀጥታ ተቀብሎ ለሸማች የሚያቀርቡበት ስርዓት በማሳለጥ በቅንጅት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የተጀመሩ አበረታች ስራዎች መኖራቸውን የጠቀሱት ወ/ሮ ሀሊማ ቅዳሜ ገበያ ብቻ ሳይሆን በሶስቱ ክፍለከተማ ገበያ በማቋቋም እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አጠናክረን እየሰራን እንገኛለን ።

ኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አቅራቢ ድርጅት (ኢት- ፍሩት) ወደ ወልቂጤ ከተማ በመግባት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልፀው ምርቶች በስፋት በማስገባት የከተማውን የኑሮ ውድነትት ለማረጋጋት አጋዥነቱ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ያሉን አማራጮችን ተጠቅመን ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በትኩረት ልንሰራ ይገባል ያሉ ሲሆን ከከተማ ነጋዴ ማህበረሰብ ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገ መሆኑ ጠቅሰው ህገ ወጥ የእህል ክምችት እንዳይኖር ቅድመ የመከላከል ስራ ላይ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑንም መገለፁን አንስተዋል።

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ንግድ ገበያ ልማት መምሪያ የእርሻ ምርቶች ግብዕይትና ጥራት አረጋጋጭ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ እሸቱ እንደተናገሩት የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የሚደረጉ ጥረቶች የሚበረታቱና ተጠናክረው መቀጠል መቻል አለባቸው ብለዋል።

የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ የህብረት ስራ ማህበራት በማጠናከር ከፍጆታ ምርቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በግብርና ምርቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።

ህብረት ስራ ማህበራት ህገወጥ ንግድ ለመከላከል ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ሲሆን አምራችና ሸማች ቀጥታ የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑ አጠናክረን በጋራ የምንሰራበት መሆን መቻል አለበት ሲሉ አቶ ወንድም ተናግረዋል።

የህብረት ስራ ማህበራት ከሰጡት አስተያየት እንደዚህ አይነት ውይይቶች ተቀራርበን ለችግሮቻችን መፍትሔ የምናስቀምጥበት ትልቅ አጋጣሚ መሆን መቻል አለበት ሲሉ አንስተዋል ።

ካነሱዋቸው ዋና ዋና ነጥቦች ህገወጥ ደላሎችን በማስወጣት ከአምራቾች ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንዲኖረን ቢደረግ ፣በቂ ካፒታል የሌለን ብድር ቢመቻችልን ፣ ትልቅ ማነቆ የሆነብን የቦታ ችግር ትኩረት ቢሰጠው እንዲሁም የባለሙያዎች ድጋፍ ቢደረግልን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በሚደረገው እንቅስቃሴ አጋዥ መሆን እንደሚችሉ ተናግረዋል ።

Previous የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚዎች የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት አማራጮች በማስፍት ዉጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo