20/2016ዓ.ም [ወልቂጤ]
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚዎች የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት አማራጮች በማስፍት ዉጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት በወልቂጤ ከተማ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ከወልቂጤ ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ጋር የውል ስምምነት ተደረገ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሰለሞን ወርቁ እንደገለፁት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ውጤታማ የሆነ ሁሉንም ዜጎች በፍትሀዊነት የጤና አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት አማራጮች በማስፍት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተናግረዋል ።
አማራጮቻችንን በማስፍት በወልቂጤ ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ጋር የውል ስምምነት የተደረገ ሲሆን ከጤና ተቋሞቻችን በላይ የሆኑ ህክምናዎች ሪፈር በማድረግ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አግባብ መፈጠሩንም ገልፀዋል።

ከሁለት ወር በላይ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የአባልነት ምዝገባ ዛሬ መጠናቀቁን ገልፀው በ2016 አመት ምህረት 14,600 በላይ አባላት መመዝገብ መቻሉንም ተናግረዋል ።
በከተማችን በሚገኙ ክፍለከተማና ቀበሌዎች ከፍተኛ ንቅናቄ በማድረግ መክፈል የማይችሉት የህብረተሰብ ክፍሎች ከተማ አስተዳደሩ በመክፈል የሚችሉት ደግሞ የአመቱ ክፍያ 1100 ብር ከፍለው አጠቃላይ 14,600 በላይ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ህብረተሰቡ ቀድሞ በከፈለው የሚታከምበት ነው ያሉት አቶ ሰለሞን በከተማ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም ከቀይ መስቀል መድሀኒቶች እንዲያገኙና ከዚህ በፊት ከተጠቃሚዎች የሚነሱ አስተያየቶች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱንም ገልፀዋል።

