
ታህሣሥ 16/2017ዓ.ም(ወልቂጤ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናዎች የመስክ ምልከታ አደረገ።

በመስክ ምልከታው የተገኙት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው እንደሀገር በወረደው ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ የተሰጠን ዕድል 198,284 በሶስት ዓመታት ወጣቱን ለማሰልጠን ገልጸው በመጀመሪያ ዓመት 50ሺህ አቅደን 23ሺህ ወጣቶችን ስልጠናው ማሳተፍ መቻሉን አብራርተዋል ።
ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ዲጂታል በሆነው አለም ውስጥ መሳተፍና መጠቀም የሚችል ዜጋን ማፍራት ያለመ መሆኑን አቶ ሰላሙ ገልጸዋል።

እንደ ሀገር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሀገራችን ያለዉ ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ዕድሉን ለዜጎች ለማዳረስ መስራታቸውን የገለጹት አቶ ሰላሙ ዕድሉን በአግባቡ መጠቀም ከዜጎች የሚጠበቅ ድርሻ በተገቢው መወጣት ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሀላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንደገለጹት በዞኑ 9,829 ሰልጣኞች ተመዝግበው ስልጠናውን እየወሰዱ እንደሚገኙና ከእነዚህም መካከል 3,380 ሰልጣኞች አለም አቀፍ ሰርተፍኬት ባለቤት ሆነዋል ብለዋል ።
ዞናችን በዲጂታላዜሽን ቀድማ እንድትገኝ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን አለም ወደዲጂታል እተመመ ባለበት በዚህ ሰዓት ወጣቱ ራሱን ከዲጂታላዜሽን አዋህዶ የበኩሉን አሰተዋጽኦ በማድረግ ሀገሩን ብሎም ከተማውን ማሳደግ ይኖርበታልም ሲሉ አመላክተዋል ።

ወጣቱ በዚህ 21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በመውሰድ የራሳችን ተፈላጊነትና ተመራጭነት በማስፋት አለምአቀፍ ተወዳዳሪ ሊሆን ይገባል ሲሉ የወልቂጤ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን ተናግረዋል ።

አክለውም በቴክኒክና ሙያ ያሉ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ማለፍ ተገቢ በመሆኑ 320 የሚደርሱ ተማሪዎች ስልጠናውን እየተከታተሉ እንደሚገኙና 100 የሚሆኑት ሰርተፍኬት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
አሁን ዲጂታላይዜሽን ያልተቀላቀለ ትውልድ የአለም ገበያው ቆሞ ስለማይጠብቀው ከጊዜው ገበያ ጋር ራስን በማሻገር መጠቀም ያስፈልጋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ኢትዮ ኮደርስ ለወጣቱ የስራ ዕድል የሚፈጥር ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸው የዲጂታል ዕቅድ ለማሳካት በ2025 ሀገራችን ከወረቀት ነጻ አገልግሎት ለመስጠት የተወጠነውን ውጥን ከግብ ለማድረስ ስልጠናው ወሳኝ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀምዱ ካሚል ገልጸዋል ።

የወልቂጤ ከተማ ማህበረሰብ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ሆኖ ኢዘዲንና መሰሎቹ ያፈራች እንደመሆኗ መጠን አሁንም በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚመጥቁ ትውልዶችን ለመፍጠር እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ።

በዕለቱም በወልቂጤ ከተማ የሚገኙ የስልጠና ጣቢያዎች በያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠናውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሰልጣኞችን ጎብኝተው በአይሲቲ ዘርፍ የሚሰሩ ስልጠናው ለመሳተፍ የተመዘገቡትን ሰልጣኞች የክልሉ ሀላፊ ማስጀመሪያ አድርገዋል ።

ወጣቱን እና ዘመኑን ለማስተዋወቅ የምትሄዱበት መንገድ የሚያስመሰግን ነዉና
፡፡ ቀትሉበት
u well come our website and to give ur apprehension
የአንተው ውጤት ነው፤
It is good technology
እናመሰግናለን
Every think are good
Very nice .I haven’t any comment.
Nice
Good