“ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ የጉራጌ ዞን እና የቀቤና ልዩ ወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤቶች በጋራ በመሆን በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የኢፍጣር ፕሮግራም አካሄዱ።

መጋቢት 8/2018 (ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞንና የቀቤና ልዩ ወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤቶች የጋራ የኢፍጣር ፕሮግራም የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እና የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድአሚን በደዊ በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ አካሂደዋል ።

በኢፍጣር ፕሮግራሙ ላይ እንደተገለፀው በተከበረውና በታላቁ የረመዳን ወር ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር በሀገሪቱ እና በክልላችን የተጀመሩ የልማትና የሰላም ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቁሟል ።

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት መሆኑ በተገለፀበት በዚህ መድረክ ህዝበ ሙስሊሙ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነቱን ማጠናከር ይጠበቅበታል ተብሏል።

በኢፍጣር ፕሮግራሙም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝዳንት ሼህ አባስ ያሲን፣ የቀቤና ልዩ ወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች፣የሁለቱ መዋቅር የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ሼሆች፣ ኡስታዞች፣ ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሁለቱ ወገኖች የተፈናቀሉ ወገኖችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

“ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት ለዘላቂ ሰላም !”

Previous ዓድዋ የአንድነት ውጤት የወንድማማችነትና የእህትማማችነት እሴት የዳበረባት አካታች፣ ሚዛናዊና ፍትሐዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል የሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን ትልቁ ማሳያ ነው -:የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo