በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር “እኔ እያለሁ አንድም ፍሬ ምርት አይባክንም” በሚል የንቅናቄ መሪ ቃል የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱና በተገቢው የተቀናጀ የምርት አሰባሰብ ስራ በቡቻች ቀበሌ በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የመሰብሰብ ስራ ተሰርቷል።

ወልቂጤ-ህዳር 9/2019ዓ.ም

በዕለቱ የምርት አሰባሰብ የከተማው አመራሮች፣ወጣት ፌደሬሽን፣ወጣት ማህበር ፣ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች፣ ተማሪዎችና ክበባቶች በአንድነት በመረባረብ የደረሱ ሰብሎችን ከማሳ ላይ በማሰባሰብ የምርት ብክነትን ለመከላከል የጋራ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት ከተማችን ሰፊ በመሆኗ በንቅናቄ የሚሰበሰብ ሰብል መኖሩ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቻችን ማየት የቻሉበት ነው ሲሉ ገልጸው፦

በከተማችን ከ470 ሄክታር በላይ በቆሎና ከ380 ሄክታር በላይ ጤፍ በበጀት ዓመቱ መዘራቱንና አጠቃላይ የግብርና ስራዎች በሰፊ እየተሰራ ያለበት ሁኔታ መኖሩን አብራርተው ከተማችን በንግዱ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በግብርናውም ላይ ሰፊ አቅም ያላት ናት ብለዋል።

ምርትና ምርታማነት ሚረጋገጠው በወቅቱ ተዘርቶ ሲሰበሰብ እንደሆነና አርሶ አደሩ ባልጠበቀው ሁኔታ ያለወቅቱ በሚዘንበው ዝናብ ምርቱ እንዳይበላሽበት በጎነት ባህላችን አድርገን ለአርሶ አደራችን አለኝታነታችን የምናሳይበት ነውም ብለዋል።

የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ እና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ በበኩላቸው የምርት አሰባሰብ ወቅት እጅግ ወሳኝና ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ማንኛውም የደረሰ ምርት በማሳ ላይ መቅረት እንደሌለበት ገልጸው፦

የምናደርጋቸው ሰው ተኮር ስራዎች የአርሶ አደሩ ገቢና የአካባቢው ኢኮኖሚ መሰረት መሆኑን ጠቁመው አመራሩ ከህዝቡ ጎን በመቆም ምርትን ከብክነት ለመታደግ የተጀመረውን ንቅናቄ እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።

የከተማው ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ ዶ/ር ወልደማረያም ዘሬ እንደገለፁት ዛሬ የተገናኘንበት ዋና ዓላማ አሁን ላይ የኢሊኖ መከሰት በከፍተኛ ጉዳት ላይ እየጣለን በመሆኑ በዚህ ወቅት ከምናከናውናቸው ተግባሮች አንዱ የአርሶ አደር ዓመታዊ ምርት መሰብሰብ ነው ሲሉ ገልፀው፦

አንደ ዞን 127 ሺ ሄክታር በላይ እንዲሁም ደግሞ በምርት ደረጃ ሲሰበሰብ ከ3ሚሊየን 336ሺ በላይ ኩንታል ይሰበሰባል ተብሎ በእቅድ ደረጃ መያዙንም ጠቁመዋል።

በአሁኑ ወቅት ያልተጠበቀ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ የደረሱ ሰብሎች እንዳይበላሹና ብክነት እንዳይከሰት አርሶ አደሩ ያለምንም መዘናጋት የራሱንና የቤተሰቡን ጉልበት ጨምሮ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም ምርቱን ከማሳ ፈጥኖ መሰብሰብ እንዳለበት ዶ/ር ወልደማረያም ዘሬ አሳስበዋል።

የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ቃልአብ ደመቀ በበኩላቸው የአርሶ አደሮችን ሰብል ለመሰብሰብ የበጋ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከሚከውኗቸው 16ቱ አገልግሎት ዘርፎች አንዱ መሆኑን ገልፀው፦

በዛሬው እለት የአንድ የአቅም ውስንነት ያለበት አርሶ አደር እህል መሰብሰብ መቻሉን በመጠቆም

በዚህም ከ60 በላይ ወጣቶች እንዲሁም የከተማና የክፍለከተማ አመራሮች የተሳተፉበት ነው ብለዋል ።

የዛሬው በጎ ፈቃድ ተግባር ለየት የሚያደርገው የ21ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በሚከበርበት ወቅት መሆኑ ነው ያሉ ሲሆን የበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አንድነታችን የምናጠናክርበትና በጎነትን የምናሰርፅበት በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

Previous በአካልና በስብዕና የዳበሩ ተተኪ ስፖርተኞች እንዲሁም ንቁ ማህበረሰብ ለማፍራት የትምህርት ቤቶች ሚና የጎላ መሆኑ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ገለፀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo