ግንቦት 20/2016ዓ.ም[ወልቂጤ ]

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የሚፈለግባቸውን መስፈርት ላሟሉ ሰላሳ አንድ ማህበራት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ርክክብ ተፈፀመ ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አቶ እንዳለ ስጦታው በርክክብ ወቅት እንደገለፁት የከተሞች የመሬት ፍላጎት ከእለት ወደ እለት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ይህን ችግር ለመቅረፍ አሰራሮችን በማዘመን ወቅቱን ያገናዘበ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም መሰረት በከተማ ደረጃ አጠቃላይ 436 ማህበራት ሲኖሩ ከእነዚህ ውስጥ ህጋዊ ሰውነት ይዘው 50 ፐርሰን የቆጠቡ 146 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ በመጀመሪያ ዙር 31 ማህበራት የግንባታ ቦታ እንዲያገኙ የማስቻል ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

ከተሠጣቸው ማህበራት መካከልም ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ የስራ ዘርፍ ለመጡ የክልል ባለሙያዎች እንዳይቸገሩ በማሰብ ለአምስት ማህበራት እንደዚሁም ለመምህራን አምስት ማህበራት በድምሩ ለአስር ማህበራት የመሬት ርክክብ መደረጉንም ክቡር ከንቲባው ገልፀዋል።

በቀጣይም ህጋዊ ሰውነት ይዘው ለቀረቡ ለክልል ባለሙያዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ከተማ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ፣የመከላከያ ሰራዊት ፣አካል ጉዳተኞች ደረጃ በደረጃ ህግና አሰራር ተከትለን በክልል በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የምናስተናግድ ይሆኖል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ እንደገለፁት የኑሮ ዘዬን ለመቀየር ከገጠር ወደ ከተማ ያለውን ከፍተኛ የህዝብ ፍሰት ቀላል አለመሆኑን በመረዳት በዞናችን በርካታ ስራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ ብለዋል።

በዚህም መሰረት በዛሬው እለት የሚፈለግባቸውን መስፈርት ላሟሉ 31 ማህበራት የመሬት ክፍፍል የተደረገ ሲሆን በቀጣይም በሂደት ላይ ላሉ ማህበራት አሰራርና ስርዓት በመከተል ተጠቃሚ የሚሆኑበት አግባብ በመፍጠር አሁን ለግንባታ መሬት የተሰጣቸው ማህበራት ከተማ አስተዳደሩ ባስቀመጠው ዲዛይን መስረት ሰርተው ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በርክክቡ ወቅት የተገኙት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዝናቡ ተካ እንደገለፁት ለከተሞች የተቀመጠውን ህግና ደንብ እንዲሁም አሰራርን ተከትሎ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ለማህበራት ያስረከበው ቦታ ለታለመለት አላማ እንዲውል የሁሉም ባለድርሻ አካል መተጋገዝ ወሳኝ መሆኑ ጠቁመው ሌሎች ከተሞች ላይ እየተደረገ ባለው ልክ ከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው ዲዛይን መሰረት መሰራት እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን በተሠጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማጠናቀቅ እንዳለበትም አስገንዝበዋል ።

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ታምራት ውድማ እንደተናገሩት የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

መሬት የተሰጣቸው ማህበራት በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት ገንብቶ ለመጨረስ ከወዲሁም ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈው ቦታው ከተረከቡ በኋላ የሚያጋጥሙ ጉድለቶች እንዳይኖሩ ተቀራርበን መወያየት ይኖርብናል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይብጌታ ንጋ እንደተናገሩት ማህበረሰባችን ከሚፈልገው ግልጋሎት አንዱ የሆነው ከከተማ ልማት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦት ነው ብለዋል ።

ከሚሰሩ ስራዎች መካከል በማህበር ተደራጅተው እና በሊዝ ካለው የህብረተሰብ ቁጥር አንፃር ተደራሽ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊትም በከተማ አስተዳደር የተሰሩ ምሳሌ ከሆኑት መካከል 95 ነዋሪዎች ቦታ ፣33 መምህራን ፣4 ለመከላከል ሰራዊት አባላት፣ለሁለት አካል ጉዳተኞች እና ለአንድ ተፈናቃይ በአጠቃላሊ135 ማህበራት ትልልፍ የተደረገባቸው ሁኔታዎች እንደነበሩ አብራርተዋል ።

በከተማ ውስጥ ከሚገኙ ማህበራት 436 ህጋዊ እውቅና ያላቸው ማህበራት ሲሆኑ 146 የሚሆኑን ደግሞ 50 ፐርሰንት የቆጠቡ መሆናቸውን ገልፀዉ አንድ ማህበር 20 ፐርሰንት ከቆጠበ እውቅና እንደሚሰጠው ተናግረዋል ።

ዛሬ በተደረገው 108 ካሬ ቦታ ለ31 ማህበራት የማስተላለፍ ስራ መሰራቱን የገለፁት አቶ ይብጌታ በጉብርየ ቀበሌ ጋሶሬ ሰፈርና ኤዋን ሰፈር መሆኑን አስድተው እያንዳንዱ ማህበር በብሎኩ የግንባታ ፍቃድ የሚሰጠው ሲሆን ከክልል በወረዱ ስታንዳርድ እና ዲዛይንና መሠረት መገንባትና ማልማት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።

እንዲሁም ከአሰራር ውጪ የሚያጋጥሙ ግንባታዎች ካሉ ማዘጋጃ ቤቱ ህግና ደንብ በጠበቀ መልኩ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ገልፀው የከተማው ወጣት በማሳተፍ የክትትልና የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

Previous የአራት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ብር በላይ የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታ የአርማታ ብረት ድጋፍ ተደረገ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo