በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት የተማሩ የቀድሞ ተማሪዎች እና የአካባቢው ተወላጆች 4,387,814 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአርማታ ብረት ስጦታ አበረከቱ።
ግንቦት 17/2016ዓ.ም [ወልቂጤ ]
የአራት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ብር በላይ የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታ የአርማታ ብረት ድጋፍ ተደረገ።

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት የተማሩ የቀድሞ ተማሪዎች እና የአካባቢው ተወላጆች 4,387,814 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአርማታ ብረት ስጦታ አበረከቱ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ እና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ጴጥሮስ አስራት እንደገለፁት የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት ለአለም እና ለሀገር የሚጠቅሙ ትልቅ አቅምና እውቀት ያላቸው ዜጎች የፈለቁበት ትምህርት ቤት ነው ብለዋል።
የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት የተማሩ የቀድሞ ተማሪዎች እና የአካባቢው ተወላጆች ላደረጉት ትልቅ አስተዋጽኦ እና ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ እና በፓርቲ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ያለው ድጋፍ ክትትል አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ ጴጥሮስ ሁለት ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ፕሮጀክቱ የማስጀመር ስራ የተሰራ ሲሆን አሁንም ለአንዳንድ ወጪዎች እንዲያግዝ የሁለት ሚሊዮን ብር በፕሮጀክቱ የሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።
የትምህርት ስራ ትውልድ የሚቀረፅበት እና የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የምናበቃበት ትልቅ ተቋም በመሆኑ ከሀገር ውስጥና ውጭ የሚገኙ የዞኑ የወላጆች እና በዚህ መልካም ስራ መሳተፍ የሚፈልጉ አካላት ሁሉ እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ራስ-ዘስላሴ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታ የኮሚቴ አባል እና ግንባታ ተካታታይ ኢንጅነር ተስፋሁን ገብሩ እንደተናገሩት ግንባታው የሚያርፈው 1300 ካሬ ላይ ባለአራት ፎቅ ህንፃ ሲሆን የተለያዩ አገልግሎት ይዘት ያለው መሆኑም ገልፀዋል።
ፕሮጀክቱ ሊሰራ የታሰበው በመንግስትና በማህበረሰብ ተሳትፎ ሲሆን የፕሮጀክቱ ግንባታ የተጀመረው ከተማ አስተዳደሩ በሰጠው የገንዘብ ድጋፍ መሆኑን ገልፀዋል።
በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና የአካባቢው ተወላጆች አሁን የተደረገው የአርማታ ብረት ድጋፍ ሰብስክትራክቸር ወይም የመሬት ስራ ማስጨረስ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ከፍት ለማድረግ የሁሉም ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ በእውቀት ፣በአይነት እንዲሁም በገንዘብ የአቅማችንን በመደገፍ የበኩላችንን መወጣት መቻል አለብን ብለዋል።
በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች እና የአካባቢው ተወላጆች ላበረከቱት ትልቅ አስተዋፅኦ ያመሰገኑት የራስ -ዘስላሴ ዋና ርዕሰ መምህር አቶ ሙባረክ ኸሊሊ እንደተናገሩት ህብረተሰቡ አሳታፊ በማድረግ ሁሉም በባለቤትነት ሊያግዝ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።
የቀድሞ ተማሪዎች ለበዓል ወደ ከተማዋ በመጡ ወቅት ጥልቅ ምክክር በማድረግ የአርማታ ብረት ስጦታ ማበርከታቸውን ገልፀዋል።

የግንባታው ፕሮጀክት ወደ ስራ በገባበት ወቅት የከተማው ወጣቶች በጉልበት ፣ እነ ክንፈ የሚባሉ ጠጠር አምራቾች 48 ሺ ብር የሚገመት ጠጠር ፣ አቶ አብርዳቸው ሱጋ መጠቅጠቂያ ብረት ቫይብሬተር ባለሀብቶች ድጋፍ እያደረጉልን ሲሆን እንዲሁም ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ሚክሰር ድጋፍ በማድረግ ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ሲሆን በየትኛው ነገር ከጎናችን ቆመው አቅማቸው በፈቀደ ልክ የሚያግዙን አካላት በማመስገን ስራው መጀመራችን ስለሆነ ሁሉም ድጋፉን ማሳየት አለበት ብለዋል።
የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ህዝቡን አነቃንቀን ስራው በታቀደለት ጊዜና ወቅት እንዲጠናቀቅ በርካታ ስራዎች ይጠበቅብናል ያሉት የራስ -ዘስላሴ ግንባታ ኮሚቴ አቶ እንድሪስ መሀመድ ለቀድሞ ተማሪዎች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የራስ -ዘስላሴ ትምህርት ቤት በርካታ ሙህራን የወጡበት ሲሆን ሁላችንም አሻራችንን አስቀምጠን ነገ ለትውልድ የሚተርፍ ስራ በመስራት በሙያዊ ድጋፍ ፣ በእውቀት፣ በሀሳብ ሁሉም የአቅሙ መወጣት አለበት ብለዋል።


Good job
amsgnalhu