በአካልና በስብዕና የዳበሩ ተተኪ ስፖርተኞች እንዲሁም ንቁ ማህበረሰብ ለማፍራት የትምህርት ቤቶች ሚና የጎላ መሆኑ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ገለፀ።

ወልቂጤ-ህዳር 10/2019ዓ.ም

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ለትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራንና ለስፖርት መምህራን ስልጠና ነክ ውይይት አካሂዷል።

በስልጠና ወቅት የተገኙት የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ቃልአብ ደመቀ እንደገለጹት በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አያያዝና አጠቃቀም፣ በማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም በተለያዩ ውድድሮች ላይ ተተኪ ስፖርተኞች በማፍራት ረገድ የታዩ ጠንካራ ጎኖችና የነበሩ ክፍተቶች በስፋት አወያይተው፦

የስልጠናው አላማ በት/ቤት ያሉ ታዳጊዎች ላይ በሚሰጠው መሰረታዊ የስፖርት እንቅስቃሴ ላይ የጋራ አቅጣጫ ለመያዝና ከተማ አቀፍ የስፖርት ውድድርን በተሻለ መልኩ በጥሩ ስነ ምግባር በበቂ ዝግጅት ጊዜ የታዳጊዎችን አቅም መመዘን በሚያስችል ሁኔታ ለመምራት ነው ብለዋል።

ብቁ፣ ተፎካካሪና ውጤታማ ስፖርተኞችን በማፍራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ለመሆን በትምህርትቤቶች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ቃልአብ አሳስበዋል።

የጽህፈት ቤቱ የስፖርት ዘርፍ ስልጠናና ክትትል ዳይሬክቶሬት አቶ አመነሸዋ ፈቀደ በበኩላቸው የስፖርት ስራዎች ግብዓት በማሰባሰብና የስፖርት መምህራን ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሚሰራ ነው ያሉ ሲሆን፦

በስልጠናውም ስፖርታዊ ጨዋነትን ማስፈን፣ የጸረ-ዶፒንግ ግንዛቤን ማሳደግ ላይ ያተኮሩ ንድፈ ሀሳባዊና ተግባራዊ ስልጠናዎች መሰጠቱንም አስታውቀዋል።

በቀጣይ ለሚካሄደው ስፖርታዊ ውድድር ተሳታፊ ስፖርተኞችን ለመመልመል በሁሉም ትምህርት ቤቶች መካከል የውስጥ ለውስጥ ስፖርታዊ ውድድር የሚካሄድ መሆኑን ገልፀው ለሁሉም ትምህርት ቤቶች ስፖርት መምህራን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

መምህራኖች በሰጡት አስተያየት ከባለድርሻ አካላት ጋር እንዲህ ተቀራርቦ መስራት ከተቻለ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተለያየ ተሰጥኦ ያላቸውና ከሱስ የፀዱ ተማሪዎች ያሉ በመሆኑ ተተኪ ስፖርተኞችን ለመፍጠር ምቹ ቦታ መሆኑን ገልፀዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይም በከተማው ያለውን የስፖርት እንቅስቃሴ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

Previous የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ በተማሪዎችና በመምህራን የሚሰሩ የሳይንስ የፈጠራ ስራዎችን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo