በ”አንትሮሽት” በእናቶች ቀን ልጆች ለእናታቸው እንዲሁም ባል ለሚስቱ ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት የሚገልፁበት፤ ምስጋናቸውን የሚያቀርቡበት በዓል ነው።

የዘንድሮው ዞናዊ የእናቶች የምስጋና ቀን “አንትሮሽት” በዓል በአበሽጌ ወረዳ አንበልታ ቀበሌ ጥር 19/2018 ዓ/ም በደመቀና ባህላዊ እሴቱ በጠበቀ መልኩ ይከበራል!!

ጥር13/2018 ዓ/ም (ወልቂጤ)

በየአመቱ በጥር ወር በደመቀ መልኩ የሚከበረው የጉራጌ እናቶች ቀን”አንትሮሽት” በዓል በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከበረ ይገኛል!!

አንትሮሽት በጉራጌ ብሄረሰብ ዘንድ ፈረንጆች “ማዘር ዴይ” ብለው ማክበር ከመጀመራቸው በፊት ለረጅም ዘመናት ሲከበር እንደነበር የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በ”አንትሮሽት” በእናቶች ቀን ልጆች ለእናታቸው እንዲሁም ባል ለሚስቱ ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት የሚገልፁበት፤ ምስጋናቸውን የሚያቀርቡበት በዓል ነው።

እለቱ እናቶች ከምንም ነገር ነፃ ሆነው ተዝናንተው የሚውሉበት፤ የትኛውንም ጥያቄያቸውንና ትዕዛዛቸውን የሚፈፀምበት፤ የተለያየ ስጦታ የሚቀበሉበት፤ በየመንደራቸው ባህላዊ ምግቦችና መጠጦች አዘጋጅተው ተሰባስበው እየበሉና እየጠጡ እየጨፈሩ ተደስተው የሚውሉበት ነው።

የእናቶች ቀን (አንትሮሽት) በየዓመቱ በጥር ወር እናቶች ለትውልድ ቀጣይነት፣ ለሀገር ሰላምና ልማት መረጋገጥ ላበረከቱት ወደር የሌለው አስተዋጽኦዋቸው ከስራ ነጻ ሆነው በባሎቻቸውና በልጆቻቸው የተለያዩ ስጦታ በማበርከት እንክብካቤ ይደረግላቸዋል።

በእለቱ ምንም አይነት ስራ አይሰሩም፤ ከየትኛውም ሃላፊነት ነፃም ናቸው።

ባሎቻቸውና ልጆቻቸው ሁሉንም ሃላፊነት ወስደው ይሰራሉ። ተሰባስበው በጋራ አክብረው ሲመለሱም ቤታቸው ውስጥ በልጆችና በባል የተዘጋጀ ሌላ ድግስና ስጦታ ይጠብቃቸዋል።

በእለቱ በዚህ ደስታ ውስጥ ሆና የምታዥጎደጉደውን የእናቱን ምርቃት የማይናፍቅ ልጅ የለም። ለልጆቿ በዋጋ የማይተመን ትልቅ ስነልቦናዊ ስጦታ ነው ምርቃቱ።

የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን

Previous የልማት ስራው በመደገፍ ቁልፍ ሚና ከሚጫወቱት የልማት ሀይሎች መካከል ልማታዊ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በከተማው ውስጥ ከፍተኛ መዋእለንዋይ በማፍሰስ እውቀትና ልምድ በማካፈል የኢኮኖሚ ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ጥረት አበረታች ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo