በለውጡ መንግስት በልዩ ትኩረት እየተሰራው የሚገኘው “ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብሳት” የአረንጓዴ አሻራ የዘመቻ ስራዎች ባህል በማድረግ ሁሉም አሻራውን ሊያኖር እንደሚገባ ተገለፀ።
ሀምሌ 24/2017ዓ.ም [ወልቂጤ ]በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በአንድ ጀንበር ከ17ሺህ በላይ ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር ተካሄደ።

በዛሬው እለት በአንድ ጀምበር እንደ ሀገር 700 ሚሊዮን ችግኝ እንደ ከተማ በአንድ ጀንበር ከ17ሺህ በላይ ችግኝ በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ቀበሌና አካባቢዎች በልዩ ዘመቻ እየተከናወነ ነው።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት እንደ ሀገር በለውጡ መንግስት በልዩ ትኩረት ኢትዮጵያ አረንጓዴ እናልብስ በተለያየ መልኩ በህዝብ ተሳትፎ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በአለም በአንድ ጀምበር ብዙ ችግኝ በመትከል እውቅና አግኝታል ሲሉም ገልፀዋል።
እንደ ሀገር ቀደምት ከነበረን የ17 ፐርሰንት የአረንጓዴ ሽፋን ወደ 23.6 ፐርሰንት ሽፋን በማሳደግ በዚህ አመት በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በልዩ ንቅናቄ የተሰራ ነው ሲሉ ከንቲባ ተናግረዋል።

በአረንጓዴ አሻራ አጠቃላይ እንደ ከተማ አስተዳደር 700ሺ ችግኝ ለመትከል ታቅዶ የተሰራ መሆኑን ያነሱት ከንቲባው እንደ ከተማችን በአንድ ጀንበር ከ17ሺህ በላይ ችግኝ ለመትከል በከፍተኛ ንቅናቄ የተሰራ ነው ብለዋል።
በአይነታቸው ለየት ያሉ ለተለያየ ጥቅም የሚውሉ ችግኞች መሆናቸውን ገልፀው የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ፣የመሬት መሸርሸር ለመከላከል የሚያስችሉ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መሆናቸውን ነው ተናግረዋል ።

ችግኞች ተተክለው ለሚፈለገው አገልግሎት እንዲውሉ በዘላቂነት በመንከባከብ እና በመጠበቅ ሁሉም በሀላፊነት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል ።
ሁሉም የከተማው ማህበረሰብ ባለው ቦታ ለምግብነት እና ውበት ያላቸው ችግኞች በአካባቢው በመትከል ወልቂጤ ከተማን አረንጓዴ አልብሰን ህዝብዋን የሚመጥን እና በሁሉም ዘርፍ ተመራጭ ሆና የስበት ከተማ እንድትሆን በጋራ መስራት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ግብር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ወልደማርያም ዘሬ እንደገለጹት እንደከተማችን በአረንጓዴ አሻራ ስራዎች የተሰሩ ያሉ ስራዎች በልዩ ቅንጅት የተሰሩ ይገኛል ብለዋል።

የምንተክላቸው ችግኞች የሚሰጡት ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ሲሉ የገለፁ ሲሆን የአፈር ለምነት ጠብቆ ለማቆየት እና ተፈጥሮዊ ጉዳቶች ለመከላከል በዚህ ዘመቻ ሁሉም ሊሳተፍ ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል ።
መትከል ብቻ ሳይሆን እንዲፀድቁ ከሙያዊ ድጋፍ ጋር ክትትልና ድጋፍ አጠናክረን መስራት አለብን ያሉት ሀላፊው ሁሉም የተከለውን መንከባከብና ለሚፈለገው ጥቅም እንዲውል የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

