ሀምሌ 23/2017ዓ.ም [ወልቂጤ ]
በ2018 በጀት አመት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በተለያዮ የስልጠና መስክ በወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እየተሰጠ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የስልጠናው አላማም አሁን ያለንበት ወቅት የቴክኖሎጂ እንደመሆኑ መጠን ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በመሙላት ከቴክኖሎጂው ጋር አብረው የሚሄዱበት መልካም አጋጣሚ ለመፍጠር መሆኑን የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀምዱ ካሚል ገልጸዋል።

በክረምት መርሃ ግብሩም መሠረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና፣ ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ና በ6 ትምህርት ዘርፍ ስልጠና ልዩ የፈጠራ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን የሚያበቃ ስልጠና ለ249ና በኢትኮደርስ 1191 ተማሪዎች ከወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና ከተማ አስተዳደሩ ት/ጽ/ቤት ጋር በመተባበር እየተሰጠ መሆኑንም አሰረድተዋል ።

በስድስት የትምህርት ዘርፍ ከሚሰጡት መካከል ጂኦስፓሻልና ስፔስ ሳይንስ ላይ ስልጠናው የሚወስዱ ተማሪዎች 10 በንድፈ ሀሳብ የተያዙ የፈጠራ ስራዎች በኮሌጁ በሚገኙ በአላቂ እቃዎች ተሰርተው የሚቀርቡበት መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይህ ስልጠና ባለፈው አመት ከነበረው የተማሪ ቁጥር ሲነጻጸር ውስንነት ያለው መሆኑን አሰታውሰው ተማሪዎች ይህ መልካም እድል እንዳያመልጣቸው የትምህርት ደረጃቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የሚከታተሉና ከዚያም በላይ ለሆኑ ተማሪዎች በነጻ ስለሚሰጥ መጥተው ስልጠናው በመካፈል የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ ሲሉ ሀላፊው ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።

በስልጠናው ተሳታፊ የነበሩት ተማሪ ሱኒ ሀይሌ ና ሀውለት ዳውድ እንደገለጹት ስልጠናው ከቀለም ትምህርታቸው ጎን ለጎን በቴክኖሎጂው ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚያግዛቸው ገልጸው

በቀጣይ እነዚህ መሰል ስልጠናው ወስደው በቴክኖሎጂው አቅማቸውን በማሳደግ ሀገራቸውን ለማገዝ እንደሚሰሩና የስራ እድል እንደሚያገኙበትም አመላክተዋል።


