“ለኢትዮጵያ ሠላም እንሩጥ”! በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር 4ተኛ ዙር ታላቁ የኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ።

“ለኢትዮጵያ ሠላም እንሩጥ”! በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር 4ተኛ ዙር ታላቁ የኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ።

የሩጫው ውድድር በኬሮድ ሰላምና ስፖርት ማህበር አማካይነት የተዘጋጀ መሆኑን ተገልጿል።

የኬሮድ ሠላምና ስፖርት ማህበር ፕሬዝዳንት አትሌት ተሰማ አብሽሮ እንዳሉት ማህበሩ በዞኑ በልማቱና በስፖርቱ ዘርፍ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ የተመሰረተ ነው።

“ለኢትዮጵያ ሠላም እንሩጥ”! በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የሩጫ ውድድር ወቅታዊ ችግሮችን በመቅረፉ አንድነትን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ጠቁመው በሩጫውም ከተጠበቀው በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈው በሠላም ተጠናቋል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው ለ4ተኛ ዙር ታላቁ የኬር ኦድ ሩጫ ላዮ የተሳተፉት አካላት ምስጋናቸውን አቅርበው ኬር ኦድ ሩጫ ባህላችንን አጉልተን ያሳየንበት፣ የመቻቻል፣ የመከባበርና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነችው ከተማችን ገፅታዋ እንዳይበላሽ ሁሉም በከተማው የሚኖረው ህዝብ ይህንን ጠብቆ ማቆየት ይኖርበታል።

ልዩነታችንን በማጥበብ በመከባበር እንዲሁም ሰላምን በማስፈን በከተማችን ላይ የምንፈልገው እድገትና ለውጥ እንዲመጣ ከመቼም ጊዜ በላይ ተቀራርበን መስራትና አንድነታችንን ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል።

በከተማው የሚስተዋሉ የልማት ክፍተቶችን ለመቀየር ባለሀብቶች፣ መንግስት እንዲሁም አጠቃላይ ነዋሪው በመተጋገዝ ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ምቹ፣ ማራኪና ውብ ገፅታ እንድትላበስ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አቶ እንዳለ ስጦታው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ በበኩላቸው በኬር ኦድ ሩጫ ለመሳተፍ ታታሪና ስራ ወዳድ ወደ ሆነው የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እንኳን ደህና መጣቹ

መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኬር ኦድ የልማትና የስፖርት ማህበር አዘጋጅነት ለኢትዮጵያ ሠላም እንሩጥ በሚል መሪ ቃል እህተማማችነት ዕሴት የማጎልበት እርስ በርሳችን የምንተዋወቅበት አንድነትን የምናጠናክርበት ነው ብለዋል።

የዞኑ ማህበረሰብ በስፖርት ልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተገኙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ለስፖርት ልማት ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀገራችን የምትታወቅበት በአትሌቲክስ ዘርፍ እየተመዘገቡ ባለው ውጤት እና እያስገኘ ባለው ጠቀሜታ የበለጠ ጎልቶ እንዲወጣ በማድረግ ስፖርት ለሰላም፣ ለፍቅር እና ለአንድነት በጋራ ቆመን በአትሌቲክስ ዘርፍ ብቁ አትሌቶችን በማፍራት በአለም አደባባይ ደምቀንና ጎልተን እንድንወጣ ሁላችንም በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቴ እንደተናገሩት የሀገራችን የስፖርት ፖሊሲ ባስቀመጠው ግልፅ አሰራር ህዝባዊ መሰረት ያለው ልማት ስራው በሁሉም አካባቢ በመዘርጋት በአለም አቀፍ ውጤት ማምጣት የሚችሉ አትሌቶች ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የሰላም፣ የመቻቻል፣ የፍቅር እንዲሁም የልማትና የአንድነት ማስፈፀሚያ ከመሆናቸው በላይ ተሳታፊዎች በዘርፉ ተጠቃሚ መሆናቸውም ተናግረዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ አባሳደር መስፍን ቸርነት በበኩላቸው የጉራጌ ዞን መቀመጫ የሆነችው ወልቂጤ ከተማ በጥሩ ሁኔታ መረጋጋት ላይ የምትገኝ ከተማ ስትሆን ለዚህ ሰላም ህዝቡና ወጣቱ በሰላም ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

አሁን እየተሰራ የሚገኘው ሰላምና ሀገራዊ ግንባታ የዞንና የከተማ አስተዳደር እንዲሁም ወጣቱ ህብረተሰቡ በቅንጅት ማስቀጠል መቻል አለበት ብለዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ በየትኛውም አለም ሀገራት ሰርተው አድረው ውጤታማ የሆኑ ፣ ሀገራቸውን አክባሪ እንዲሁም ያላቸውን አካፍለው የሚኖሩ ማህበረሰብ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል ።

በአትሌቲክስ ዘርፍ በዞኑ በርካታ የሀገራችንን ሰንደቅ ከፍ ማድረግ የቻሉ አትሌቶች የወጡበት መሆኑን ገልፀዉ በዚህ ተግባር እየተሳተፉ ያሉ አካላትን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ሰላምንና አንድነትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በውድድሩ እንደተሳተፉ አንስተው ውድድሩ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።

በ15 ኪሎ ሜትር በተሸፈነው በዛሬ ውድድር

በሴቶች ዘርፍ

1.መብርይ ግደይ የወርቅ ሜዳሊያ (ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

2.መቅደስ ሺመልስ ብር ሜዳሊያ (በግል )

3. ጉተን ሽንቆ የነሀስ ሜዳሊያ (ከኦሮሚያ ፖሊስ)

በወንዶች ዘርፍ

1. ቸምቤሳ ደበላ የወርቅ ሜዳሊያ (በግል)

2.ዘነበ አየለ ብር ሜዳሊያ (ከዘቢደር አትለቲክስ ስፖርት ክለብ)

3.ጃክሳ ታደሰ የነሀስ ሜዳሊያ(በግል )

በፕሮግራሙ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን፣ የወልቂጤ ከተማ አመራሮች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

Previous ታላቁ የኬር ኦድ ሩጫ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ይካሄዳል

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo