የፊታችን ሀምሌ 14/2016ዓመተ ምህረት በወልቂጤ ከተማ የሚካሄደው ታላቁ ኬር ኦድ ሩጫ አራተኛ ዙር 2ተኛው ጋዜጣዊ መግለጫ ተደረገ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው እንደገለፁት ኬር ኦድ ሩጫ እንደ ቃሉ መረዳት እንደምንችለው ሰላም ተናገረ ስለ ሰላም አብስር በመሆኑ ሁላችንም ለከተማችን የሰላም ግንባታ በጋራ የምንሰራበት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ከተማችን በርካታ መድረኮች ማስተናገድ የቻለች በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ብላ ሰላም ወዳድ ማህበረሰብ የሚኖርባት ከተማ መሆኑዋን አሳይታለች ብለዋል።
በኬር ኦድ ታላቅ ሩጫ 10 ሺ ህዝብ ይሳተፋል ያሉት ከንቲባው የከተማችን ማህበረሰብ በተለመደ እንግዳ መቀበያ እሴቱና ባህሉ ” የተንቢ” ብሎ ለመቀበል ዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ሩጫው በከተማችን መካሄዱ ያለው አስተዋጽኦ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከፍተኛ ሲሆን ህዝባችን ይህን በመረዳት ለከተማችን መልካም ገፅታ የበኩላችንን በመወጣት ሁሉም በነቂስ በመውጣት ባህላችንን እሴታችንን ለዓለም በማስተዋወቅ ማህበረሰባችንን የሚመጥን ስራ በጋራ መስራት መቻል አለብን ብለዋል።
የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከር ወንድማማችነትን ለማጎልበት ዓላማ የተደረገበት ነው ያሉት ከንቲባው ስፖርትን ባህል ከማድረግም በተጨማሪ ከተማውን በኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ ያለው ምቹነት ለማስተዋወቅም ያግዛል ተብሏል።
ከጸጥታውም አንጻር ከፌደራል ከክልል፣ ከዞኑን ከከተማው አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ቅድመ ዝግጅቱ መጠናቀቁና ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ያለምንም ስጋት እንዲሳተፍ ጥሪ ተላልፏል።
በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ቅድመ ዝግጅት መጠናቁንና ምንም አይነት የፀጥታ ችግር ሳይኖር ሩጫ እንደሚካሄድ ገልፀው ወጣቱም ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ ለከተማዋ ሰላም ግንባታ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ለከተማዋ ፀጥታ በባለቤትነት ሊያግዝ ይገባል ብለዋል።

ኬር ኦድ የልማት ስፖርት ማህበር መስራች አትሌት ተሰማ አብሽሮ በመግለጫው እንደተናገሩት ኬር ኦድ ሩጫ ማህበረሰቡን ከስፖርት ጋር በማስተሳሰር ባህልና እሴት በማስተዋወቅ ባለፉት ሶስት አመታት ከፍተኛ ስራ መስራቱን ተናግረዋል።
በዘንድሮ አመት ከ600 በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አትሌቶች የሚሳተፍ ሲሆን የሀገራችን ትላልቅ የፌዴራል እና የክልል ክለቦች በስፍት እንደሚሳተፉበት አብራርተዋል ።
ከ2: 00 ሰዓት የሚጀመረው መነሻውን ከወልቂጤ ዩንቨርስቲ እስከ ወልቂጤ ከተማ 15 ኪሎሜትር ርቀት ያለው መሆኑን የገለፁ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓት የዊልቸር ውድድሩ በማካሄድ የማህበረሰብ ደግሞ 2:45 ላይ እንደሚጀመር ገልፀዋል።
ከዚህ በፊት በኬር ኦድ ሩጫ ላይ ተሳትፈው ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን አንስተዋል ።
በዘንድር የኬር ኦድ ሩጫ ላይ ተሳትፈው ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች ከፍተኛ ሽልማት በማዘጋጀት በአለም አቀፍ ደረጃ ተሳታፊዎች ሆነወ ሀገራቸውን ማስጠራት የሚችሉ አትሌቶች የምናወጣበት ነው ብለዋል።

ኬር ኦድ ሩጫ እንደ ሀገር አቀፍ በየጊዜው ተቀባይነት እየጨመረ የመጣው ማህበረሰባችን ባሳየው መልካም የእንግዳ ተቀባይነቱ መሆኑን አንስተው ማህበረሰባችንም በነቂስ በመውጣት እንግዶቻችንን በመቀበል ያለውን እሴትና ባህል እያስተዋወቀ የከተማው መልካም ገፅታ የምናሳይበት ትልቅ አጋጣሚ ነው ሲሉ አትሌት ተሰማ አብሽሮ ገልፀዋል::
መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተቀመጡገ ሊኮች በመጫን የተቋማችንና ሌሎች የሚዲያ አማራጮችን ይጠቀሙ፡





