እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
ወሄም ሳረናሁም ! ወሄም እማትሜ ሳረንደም!

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት፣ በሁለት ዘርፍ አንደኛ በመዉጣት የዋንጫ እና ልዩ ተሸላሚ ሆኖአል።
≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡
መስከረም 9/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)
የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት እቅድ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ የምክክር መድረክ በዛሬው እለት አካሂደዋል።
በዚህም የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ፣የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ባጠቃላይ ከዞኑ ካሉ ከተሞች 1ኛ በመውጣት የዋንጫ፣የሰርተፍኬት፣ተሸላሚ መሆን ችሏል።

በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ በንቅናቄ እንዲመራ የተደረገዉ የ5 ሚሊየን ኮደሮች ኢንሼቲቭ በማስመዝገብ፣ስርቲፋይ በማድረግ ከዞኑ ካሉ ከሁሉም መዋቅር 100% እና ከዛም በላይ በማምጣት የ cat 6 network cable እንዲሁም ሙሉ የጥገና toolkit እና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኖአል።


