በጉራጌ ዞን መዲና በወልቂጤ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ

በጉራጌ ዞን መዲና በወልቂጤ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ‼️

ታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ነገ ሀሙስ ከጠዋቱ 12:30 ሰዓት ጀምሮ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ይካሄዳል።

መስከረም 7/2018ዓ.ም (ወልቂጤ)

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪነት “በሕብረት ችለናል” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት ድጋፋቸውና ደስታቸውን ይገልፃሉ።

‎እንዲሁም የታላቁን የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ባሳተፈ መልኩ ከጠዋቱ 12:30 በራስ-ዘ-ስላሴ ትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ መናኸሪያ ድረስ የሚካሄድ ሲሆን በአንድነት ሁሉም ደስታውን የሚገልፅበት ነው።ብልፅግና ፓርቲ ከተወለደ ጊዜ ጀምሮ በሀገራችን በርካታ ተጀምረው የቆሙ እና አዲስ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በመጨረስ በአፍሪካና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተቸረው ፓርቲ ሲሆን ለዚህም ትልቁ ምስክር የህዳሴ ግድብ ነው።

‎በሁሉም እድሜ ክልል የሚገኝ ኢትዩጵያዊ የተገነባው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ነገ በምናደርገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ሁላችንም ተገኝተን ድጋፋችንና ደስታችን በጋራ እንገልፃለን ።

‎በዚህም በተዘጋጀው የድጋፍና የምስጋና ሰልፍ ላይ ከክልል ጀምሮ እስከ ከተማው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጨምሮ የከተማዋ ነዋሪ የሚሳተፍበት ይሆናል።

Previous በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የፊታችን ሀሙስ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለምርቃት በመብቃቱ የድጋፍ ሰልፍ እንደሚካሄድ ተገለፀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo