የኢንተርፕራይዞችን ልማት ለማፋጠንና ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ።

የወልቂጤ ከተማ አሰተዳደር ስራዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት የ1ኛ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት አቅርቦ ሰፊ ውይይት ተደጓል።

ታህሳስ 24/2017ዓ.ም [ወልቂጤ]

የኢንተርፕራይዞችን ልማት ለማፋጠንና ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ።

የወልቂጤ ከተማ አሰተዳደር ስራዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት የ1ኛ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት አቅርቦ ሰፊ ውይይት ተደጓል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት በመመሪያና ደንብ መሰረት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተናበበና የተቀናጀ አሰራር መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው

የስራ አጥ ልየታ ላይ የተሰራውን የተጠናከረ ተግባር ሥራ ዕድል የመፍጠር ሂደቱም ላይ ሊደገምና ብድርና ሼዶች በማስመለስ ሂደት ለወጣቱ ሥራ ሊፈጠርለት ይገባል ሲሉ ገልፀው።

ሁሉም የድርሻውን ወስዶ ከሰራ የስራ እድል የማይፈጠርበት ምክንያት አይኖርም ያሉት ከንቲባው የህብረተሰቡን ፍላጎት ያማከለ ስራዎችን መሰራት አለብን ሲሉም አመላክተዋል።

የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙራድ ያሲን እንዳሉት የስራ ዕድል መፋጠር ቀላል የሚባል ነገር ባለመሆኑ ሁሉም የድርሻውን ወስዶ ከሰራ ከተማው ላይ የሚስተዋለው የብድር አመላለስ ችግር መቅረፍ ይቻላል ያሉ ሲሆን

የትኛውም አካል የወሰደው ብድር የመመለስ ግዴታ አለበት ሌላው ወጣት በእድሉ መጠቀም ስለለበት ሲሉ አብራርተዋል።

የስራ እድል ፈጠራ ስራው ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ባለመሆኑም ሌሎች ከዞን እስከ ወረዳ ያሉ የመንግስት ተቋማት ከስራቸው ባህሪ አኳያ የስራ እድል ፈጠራ ስራን አቅደው በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ እንደገለፁት አንድን ነገር ስንጀምር ለመጨረስ መሆን መቻል አለበት ለማህበረሰቡ ይጠቅማል ብለን የጀመርናቸውን ነገሮች በተግባር መጨረስ ይገባል ሲሉ ገልፀው።

ማህበረሰቡም ለምንሰራው ሥራ አጋዥ እንጂ አደናቃፊ መሆን የለበትም የተወሰደ ብድር በአግባቡ መመለስና ሌሎች ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማስቻል ሥራ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ጴጥሮስ አስራት በበኩላቸው በየደረጃው ያሉ ሁሉም አካላት የችግሩ ባለቤት በመሆን የተለዩ ችሮችን በቁርጠኝነት ይዞ ለተግባራዊነቱ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አሰተዳደር ስራዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ትግስቱ ተኸልቁ እንደገለፁት በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድና በቅንጅት እንደሚሰራም ጠቁመው።

ሼድና የገንዘብ ብድር አመላለስን በተመለከተ መረጃዎችን አጥረተን ጨርሰናል በቁርጠኝነትና በመተጋገዝ ሁሉም የድርሻውን በመወጣት ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከተሳታፊዎች ከተነሱ ሀሳቦች መካከል የወጣቶች የተዘዋዋሪ ፈንድ ብድር አመላላስ ውስንነት መኖሩ፣ የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎች ቁጥር አናሳ መሆን፣ ሼዶች ለማህበራት በፍትሃዊነት አለማስተላፍ መኖሩና ሌሎችም ጥያቄዋችና አስተያየቶች ተነስተው ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመድረኩም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ ስብሰባው ተጠናቋል።

Previous ጀፎረ የጉራጌ የመንደር አመሰራረት መሰረት ባደረገ ባህላዊ ይዘት ሳይለቅና እሴቱን አስጠብቀን ለመስራት የገጠር የኮሪደር ልማት ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው :-የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo