
ታህሳስ 23/2017ዓ.ም [ወልቂጤ ]
ጀፎረ የጉራጌ የመንደር አመሰራረት መሰረት ባደረገ ባህላዊ ይዘት ሳይለቅና እሴቱን አስጠብቀን ለመስራት የገጠር የኮሪደር ልማት ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው :-የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት “ጀፎረ ባህላዊ የምህንድስና ጥበብ ” በሚል መሪ ቃል በጉብሬ ክፍለከተማ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ቡቻች፣ኤዋንና ጋሶሬ የገጠር ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት እንደ ሀገር በተለየ መልኩ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ በከተማ አስተዳደሩ በሁለት ዙር መልማት በሚችሉ ቦታዎች በመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመስራት በንቅናቄ አመራሩና ህዝቡ ባሳተፈ ሁኔታ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በመጀመሪያ ዙር 17ኪሎሜትር የሚሰራው የኮሪደር ልማት ስራ እቅድ ታቅዶ ወደ ሀብት አሰባሰብ ላይ እየተገባ ይገኛል ያሉ ሲሆን የከተማው ህዝብ ለልማት ያለውን ፍላጎት ያሳየበት ነው ተናግረዋል።
የገጠር ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት “ጀፎረ” በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች መካከል በቡቻች ቀበሌ የማስጀመር ስራ የተጀረበት አግባብ መኖሩን ጠቁመዋል ።

ማህበረሰቡ ለጀፎረ ያለው ክብር ያሳየበትና ትላንት አባቶቻችን ሳይማሩ የምህንድስና ስርዓት ይዘው ጠብቀውና አስጠብቀው ህግና አሰራር ዘርግው ያቆይቱን ጠብቆ ማቆየት ይገባል ብለዋል።
ጀፎረ የጉራጌ የመንደር አመሰራረት መሰረት ባደረገ ባህላዊ ይዘት ሳይለቅና እሴቱን አስጠብቀን ለመስራት የገጠር የኮሪደር ልማት ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ የተጀመረው የከተማ የኮሪደር ልማት ስራ ህዝብ ባሳተፈ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

የገጠር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እንደ ሀገር መነሻ ተደርጎ እየተሰራ ያለው የጉራጌ ጀፎረ ነው ያሉ ሲሆን ከአባቶቻችን የወረስነው የመንገድ አሰራር ጠብቀን ማቆየት በሚያስችል መልኩ መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን የህዝቡም ተቀባይነት ከፍተኛ ነውም ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሪት ትግስት ይርጋ እንደተናሩት ለጉራጌ መንደሮች ትልቅ ውበት መላበስ ምክንያት ባህላዊ የጀፎረ አሰራር በመሆኑ ሁላችን ጠብቀን ማቆየት ይጠበቅብናል ብለዋል።

እኛ ያለንን ሀብት ሳናውቅ አለም የተረዳበት አግባብ በመኖሩ መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት መሰረት እንደባለቤት ብዙ መስራት የሚጠበቅብን ሲሆን የገጠር ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የጉራጌ ለአውራ መንደር ጀፎረ ትልቅ ትኩረት የሚሰጥበት ዋና ምክንያት በብሔረሰቡ ሰርግ ፣ደስታ፣ ሀዘን፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የጋራ መፍትሄ የሚሰጥበት መድረክ በመሆኑ ይዘቱ ሳይለቅ ከአያቶቻችን ያገኘነው ትልቅ የምህንድስና ጥበብ ለቱሪዝም መስህብነት እንዲውል ማስቻል ይጠበቅብናል ብለዋል።

በንቅናቄ መድረኩ የተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የጉራጌ ጀፎረ ባህላዊ ይዘቱ ሳይለቅ ጠብቆ ለማቆየት የገጠር ኮሪደር ፕሮጀክት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
በመንግስት የተጀመረው የገጠር ኮሪደር ልማት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ባላቸው አቅምና እውቀት እንደሚያግዙ ተናግረዋል ።


ጀፎረ የቀድሞ አባቶች ያለ ምህንድስና ጥበብ ለዘመናት ጠብቀው ያቆዩትን አሁን ላይ በተለያዩ ሁኔታዎች ይዘቱን በመቀየር ለአደጋ እየተጋለጠ በመሆኑ ሁላችንም በመንከባከብና በመጠበቅ በአጭር ጊዜ ወደ ነበረበት ለመመለስ እንደ ከተማችን በሚገኙ ቀበለያት ዛሬ የተጀመረው የንቅናቄ መድረክ እዛው ጀፎረ ላይ መደረጉ አመላካች ነው