የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የገቢ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ ።

ሰኔ 14/2016ዓ.ም [ወልቂጤ ]

የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የገቢ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገቢ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በበጀት አመቱ ለከተማው የገቢ አቅም ለማሳደግ በንቅናቄ የተሰሩ የገቢ አሰባሰብ እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አቶ እንዳለ ስጦታው እንደገለፁት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ያሉንን የገቢ አማራጮች በአግባቡ አሟጠን መጠቀም ስንችል ነው ሲሉ ገልፀዋል ።

ከንቲባው በኔዘርላንድ በነበራቸው የስራ ጉብኝት ያገኙትን የገቢ አሰባሰብ ተሞክሮ ሰነድ በማቅረበ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።

በከተማው በመንግስትና በህዝብ በቅንጅት የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች አበረታች ውጤቶችን በማስቀጠል በህዝብ የሚነሱ የመልማት ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ በገቢ አሰባሰብ ሥርዓት በማስፈፀም ሂደት የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች የመለየት ስራ ተጠናክሮ በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ ገልፀዋል ።

በእውቀት የተደገፈ ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂና ፈጠራን በመጠቀም መጀመሪያ የገቢ አቅማችንን በማሳደግ ስማርት ሲቲ ለመገንባት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል ይጠበቃል ሲሉ ከንቲባው አሳስበዋል ።

እንዲሁም ልማታችን እንዳናሳልጥ እንቅፋት የሚሆኑብን ችግሮችን ተቀራርበን እየፈታን ለከተማችን ሰላምና ፀጥታ ህዝቡና የፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።

የወልቂጤ ከተማ ገቢ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብድልከሪም መሐመድ እንደገለፁት በገቢ አሰባሰብ ንቅናቄ በሶስቱ ክፍለ ከተማ ከዓምና በተሻለ መልካም አፈፃፀም የታየበት እንደነበረ አንስተው የገጠሙ ችግሮችም ለቀጣይ እንደ ግብዓት በመውሰድ የተመዘገቡ ውጤቶች ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል ።

በ2016 በጀት ዓመት የ11 ወር ከመደበኛ ገቢ ብር 442,476,116 ለማሰባሰብ ታቅዶ ብር 351,714,557.59 በመሰብሰብ የእቅድ 85 ፐርሰን መፈፀም መቻሉን ጠቁመው ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነፃፀር በብር 74,912340.4 ብልጫ መኖሩንም አብራርተዋል ።

በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ገቢ ብር 93,413,800 ብር ይሰበሰባል ተብሎ ታቅዶ 73,654,10374 በመሰብሰብ የእቅዱ 79 ፐርሰንት መፈፀም መቻሉ ገልፀው ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነፃፀር በብር 34,842,702.02 በብልጫ መሰብሰቡ ተናግረዋል።

በከተማዋ የገቢ አሰባሰብ በሚጠበቀውና በሚፈለገው ልክ ውጤት ማስገመስገብ አለ መቻሉን የገለፁት አቶ አብድልከሪም የሁሉም ባለድርሻ አካል ርብርብ ከፍተኛ መሆን መቻል አለበት ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በነበረው የገቢ አሰባሰብ ንቅናቄ መልካም አፈፃፀም የታየበትና ከተማዋ መጠቀም ባለባት ልክ ተጠቃሚ ባለመሆኗ የህዝቡ የልማት ስራዎች ምላሽ መስተጓጎል ማሳያ መሆንንም አንስተዋል።

ከግብር አሰባሰብ ችግር ባሻገር የተጣራ መረጃ በሰነድ የማደራጀት ስራ በመስራት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ ስራ በመስራት ከተማዋን የሚገባትን ግብር መሰብሰብ መቻል እንዳለበትም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የከተማዋ ልማትና እድገት የሁላችንም በመሆኑ ለትውልድ የሚተላለፍ ስማርት ሲት በመገንባት ያሉን የገቢ አማራጮቻችን በማስፋት የትኛውንም ግብር ከፋይ የሚጠበቅበትን በመክፈል ግዴታውን መወጣት መቻል እንዳለበት አስገንዝበዋል ።

የሰላምና የፀጥታ ስራ ሁሉም ባለቤት ሊሆን ይገባል ያሉት ተሳታፊዎች የተሻለች ከተማን ለመፍጠር ህዝቡና የፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ግብር ከፋዮች የተጣለባቸውን የዘመኑ ግብር በወቅቱና በታማኝነት እንዲከፍሉ ከማድረግ ጎን ለጎን የንግድ ስራ ፍቃድ እድሳት ስራ ላይ በቅንጅት መስራት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ከመድረኩ ተገልጿ ተጠናቋል።

Previous 1 ሺህ 4 መቶ 45ኛው የኢድ-አል አድሃ [አረፋ] በዓል በወልቂጤ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo