በወልቂጤ ከተማ እየተሰራ ያለው 25 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ የጉራጌ ዞንና የወልቂጤ ከተማ አመራሮች በተገኙበት የእስካሁኑ አፈጻጸም ተገምግሟል።

ሚያዝያ 15/2017(ወልቂጤ )

በወልቂጤ ከተማ እየተሰራ ያለው 25 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ የጉራጌ ዞንና የወልቂጤ ከተማ አመራሮች በተገኙበት የእስካሁኑ አፈጻጸም ተገምግሟል።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር እየተሰራ ያለው 25 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ሥራ በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በማጠቃለያ ንግግራቸው አመራሩ የሀብት አሰባሰብ ስራ የቅድሚያ ተግባሩ በማድረግ በትኩረት እየሰራበት የሚገኝ ሲሆን ቀጣይም የገቢ አማራጮችን ማስፋት ያስፈልጋል ብለዋል።

በቀጣይም ያልፈረሱ ቤቶች ካሉ ማፍረስ ፣ የፈረሱትም ደግሞ ማዘጋጃ ቤቱ በሰጠው ዲዛይን መሰረት ብቻ መገንባት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ አቅጣጫዎች አስቀምጧል።

አቶ ላጫ አክለውም በኮሪደር ልማቱ ላይ አደናቃፊ ችግሮች ሲኖሩ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ፣ችግሮችን በማረም ጊዜውን ያማከለ ስራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ስራው በተቀመጠለት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ጊዜ የለኝም በሚል እሳቤ ቀንና ማታ እየተሰራ ያለው ስራ ይበልጥ መዳበር እንዳለበት አብራርተዋል።

የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ እየሰጡ መሄድ ይገባል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው።

ይህ የኮሪደር ልማት የዞኑ መንግስትና የከተማ አስተዳደሩ ተግባሩ ግንባር ቀደም በማድረግ ትኩረት የተሰጠው ወቅታዊ አጀንዳ ስለመሆኑ የገለጹ ዋና አስተዳዳሪው የማህበረሰቡ ተሳትፎ ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም መልእክት አስተላልፏል።

በመድረኩም የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስከያጅ አቶ ቶፊቅ ሱልጣን የእስካሁኑ የስራ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የክልሉ መንግስት በከተማው 25 ኪሎ ሜትር የኮርደር ልማት እንዲሰራ ፕላን አድርጎ ከሰጠው በመጀመሪያ ምራፍ በ4ቱም ሳይቶች 17 ኪሎ ሜትር ውል በመግባት ተግባሩ በጥሩ ሁኔታ በመከናወን ላይ ይገኛል።

የዚህ አካል የሆነው በከተማው በፌደራል መንግስት ERA የሚሰራው የ5 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ስራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ እና ቀሪ ስራዎች በቀጣይ እንደሚሰሩ አብራርተዋል።

የተከተማው ማህበረሰብ የኮሪደር ልማት ሥራው ውጤታማ እንዲሆን ልማቱ በሚከናወንበት አካባቢ ንብረታቸውን በማንሳትና፣ይዞታቸውን በመልቀቅ ፣ገንዘብ በማዋጣት እና በበጎ ፍቃደኝነት የበኩላቸውን እየተወጡ ያለው ስራ እጅግ አበረታች መሆኑ ገልጿል።

የኮሪደር ልማቱ 25 ኪሎ ሜትር እንደሚያካትት ገልጸው፣ ልማቱን ውጤታማ ለማድረግም ህዝብን በማወያየት ፣በማሳተፍና መብታቸው በማስጠበቅ እንደሆነ ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማት ሥራው በከተማው በአራት ሳይቶች ተለይቶ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።

እነዚህም ከአደባባይ እስከ ኮሌጅ፣ ከአፓርታማ እስከ ጉብሬ አደባባይ፣ ከጉብሬ አደባባይ ታች ገበያ ወይም መስጊድ እና ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እስከ ጉብሬ አደባባይ ድረስ ያካተተ ስመሆኑ አንስተዋል አቶ ቶፊቅ።

በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ከአስተዳደሩ እና ከማህበረሰቡ ተሳትፎ ለመሰብሰብ ታቅዶ በተለይ በሚዲያ ቻሌንጁ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑ ተናግሯል።

ኮሪደር በሚሰራባቸው አካባቢዎች የውሃ ፣የቴሌ የመብራት እና መሰል ከአገልግሎት ሰጪ ተቋሟት ጋር በመግባባት የልየታ እና አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸው አመላክቷል።

ለአብነትም ከአደባባይ እስከ ኮሌጅ ያለው አጠቃላይ የመብራት ፖል ስራ በአፈጣኝ እንዲጠናቀቅ እና ቀሪ ውስን ስራዎችም ካሉ ወደ ተግባር እንዲሚገባ አመላክቷል።

የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።

Previous ህዝበ ክርስቲያኑም ከኢየሱስ ክርስቶስ ትህትናንና ፍቅርን በመማር በበዓል ወቅትም ሆነ በሌላ ጊዜ መተጋገዝንና አብሮነትን በማጎልበት ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በፍቅር መኖር እንዳለባቸውም አሳስበዋል

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo