ህዝበ ክርስቲያኑም ከኢየሱስ ክርስቶስ ትህትናንና ፍቅርን በመማር በበዓል ወቅትም ሆነ በሌላ ጊዜ መተጋገዝንና አብሮነትን በማጎልበት ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በፍቅር መኖር እንዳለባቸውም አሳስበዋል

May be an image of 1 person and text

ሚያዝያ 1O/2O17 ዓ/ም [ወልቂጤ]

ህዝበ ክርስቲያኑ የትንሣኤ በዓልን ሲያከብር በመረዳዳትና አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አሳሰቡ።

ከንቲባው ለመላው የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫቸውንም አስተላልፈዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር የትንሣኤ በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት የትንሣኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበርና ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅርን ያሳየበት በዓል መሆኑን ገልፀዋል።

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ዕለት የሚታሰብበት ዕለት ነው።

በዓሉም እግዚአብሔር አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ታላቅ ፍቅር በልጁ ሞትና ትንሣኤ የገለጠበት በመሆኑ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እጅግ ታላቅ በዓል ተደርጎ ይታያል።

ህዝበ ክርስቲያኑም ከኢየሱስ ክርስቶስ ትህትናንና ፍቅርን በመማር በበዓል ወቅትም ሆነ በሌላ ጊዜ መተጋገዝንና አብሮነትን በማጎልበት ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በፍቅር መኖር እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በአሉ ከራስ ይልቅ ለሌሎች መኖርን የሚያስተምር መሆኑን ጠቁመው አንዳችን ለአንዳችን ሠላምና አብሮነትን ልንከፍል የሚገባው ዋጋ ምን ያህል ትልቅ መሆኑን ያስተምራል ብለዋል።

ስለሆነም የትንሣኤ በዓል በምናከብርበት ወቅት ከጥላቻ በመራቅና በጎነትና ፍቅርን በመግለጽ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተለይ በበዓል ወቅት ያለው ለሌለው በማካፈል በመረዳዳትና አብሮነትን በማጠናከር መሆን አለበት ያሉት ክቡር ከንቲባው የትንሣኤ በዓል ሲከበርም አቅመ ደካሞችንና ጧሪ ያጡ ወገኖችን በማገዝ መሆን አለበት ብለዋል።

በከተማው የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጨምሮ በርካታ የልማት ስራዎች በመንግስትና በኅብረተሰብ ተሳትፎ እየተከናወኑ መሆናቸውን ክቡር ከንቲባው ጠቅሰው ኅብረተሰቡ ለበዓል በሚሰባሰብበት ወቅት በልማቱ ጉዳይ መምከር እንዳለበትም አሳስበዋል።

ለኮሪደር ልማት ስራው ኅብረተሰቡ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለፁት ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ሁሉም ኅብረተሰብ ወልቂጤ ከተማ ውብና ፅዱ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን አቅም በፈቀደው ልክ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

Previous በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎሮሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ከትምህርት ጽህፈት ቤት ጋር በጋራ በመሆን “ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሁለንተናዊ ሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ የፈጠራ ስራ ውድድሮች ሽልማትና የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo