በከተማው ውስጥ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስክ የፈጠራ ስራዎችን በማጎልበት ውጤታማ የኢኖቬሽን ና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖርና ተማሪዎች ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ያላቸውን ቅርበት ለማሳደግ የሳይንስ ሳምንት በትምህርት ቤቶች መከበሩ አጋዥ መሆኑን አንስተዋል።

አክለውም በሳይንስ ዘርፍ በቂ ድጋፍ ተደርጎ በቴክኖሎጂ የታነፀ ትውልድን በማፍራት ሀገራችንን ከሌሎች ሀገሮች ተወዳዳሪ ማድረግ ለሀገራችን እድገት መስራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች በሚፈለገው ልክ ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲችሉ ሁሉም የድርሻውን ወስዶ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ።

የካቲት 25/2018ዓ.ም [ወልቂጤ]

በጉራጌ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤትና ከትምህርት ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር “በሳይንስና ቴክኖሎጂ የዳበረ ትውልድ በመፍጠር የቀጣይ ዲጂታላይዜሽን ጉዞ እውን እናድርግ ” በሚል መሪ ቃል የ2018 አመታዊ የሳይንስ ሳምንት በራዘ-ስላሴ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከበረ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና የቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀምዱ ካሚል እንደገለፁት የሳይንስ ሳምንት ዓላማ በሳይንስ ትምህርት ዘርፍ የተማሪዎች የመማር በፍላጎት እየቀነሰ ስለመጣ የሳይንስ ዘርፍ ላይ መነሳሳት እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።

በከተማው ውስጥ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስክ የፈጠራ ስራዎችን በማጎልበት ውጤታማ የኢኖቬሽን ና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖርና ተማሪዎች ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ያላቸውን ቅርበት ለማሳደግ የሳይንስ ሳምንት በትምህርት ቤቶች መከበሩ አጋዥ መሆኑን አንስተዋል።

አክለውም በሳይንስ ዘርፍ በቂ ድጋፍ ተደርጎ በቴክኖሎጂ የታነፀ ትውልድን በማፍራት ሀገራችንን ከሌሎች ሀገሮች ተወዳዳሪ ማድረግ ለሀገራችን እድገት መስራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

የሳይንስ ሳምንት መከበሩ በትምህርት ቤቶች የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሀሳባቸው እውን ሆኖ ሀገር መቀየር እንዲችል ለማስተዋወቅ ና በቀጣይ ለሚደረገው ኤግዚቢሽን እንዲዘጋጁ ለማስቻል ነው ሲሉ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ሀላፊ ተወካይ አቶ አብይ ወልደሰንበት ተናግረዋል።

የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች በሚፈለገው ልክ ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲችሉ አጋዥ አካላትን በማስተባበር ና ከሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጋር ትስስር እየተፈጠረ ስራዎቹን ለማስፋትና የፈጠራ ባለቤቶችን ለማበረታታት እንደሚሰሩም አቶ አብይ ጠቁመዋል ።

ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች በተማሪዎችና መምህራን መቅረባቸውን በተለይም በሰው ሀብት መረጃ አያያዝ ዘርፍ የተሰራው ወቅታዊና ሀገር የምትፈልገው የሰው ሀብት ችግር የሚቀርፍ ነው ሲሉ አቶ ደምስ ፈቀደ የከተማ ትምህርት ጽህፈትቤት ተወካይ ናቸው።

ትምህርትቤቶች ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን የፈጠራው ስራ ለማገዝ በበጀት ተደግፎ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ደምስ እንደ ሀገር በፈጠራው ዘርፍ በትኩረት እየተሰራ እንደመሆኑ በከተማ ደረጃ የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ሁለም ባለድርሻ አካል በመተጋገዝ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራት ይኖርብናልም ብለዋል።

በትምህርት ቤቱ የሳይንስ ሳምንት ሲከበር በእለቱ የተገኙ እንግዶች ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ የፈጠራ ባለቤት ተማሪዎች የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ጉብኝት ተደርጓል።

እለቱም አስመልክቶ በሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዶ አሸናፊ ተማሪዎች እና በፈጠራ ስራ ለተሳተፉት ትምህርትቤቶች የእውቅና የሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Previous በጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲው ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት “የስንዴ ነዶ” የማስተዋወቂያና የርክክብ መድረክ ተካሂዷል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo