የካቲት 20/2018(ወልቂጤ)

በዞኑ በፓርተው እሳቤ የተጀመሩ ስራዎች ይበልጥ በማጠናከር ብልጽግና ለማጽናት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
ይህ የተገለጸው በጉራጌ ዞን ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በወልቂጤ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ የዛሬው መድረክ የጉራጌ ዞን እግር ኳስ ክለብ የክልሉ ሻምፒዮን በሆነበትና ውድድሩን በበላይነት ባጠናቀቀበት ወቅት በመሆኑ ለየት ያደርገዋል።
የጉራጌ ዞን ከብዙ አመታት በኃላ ዋንጫው አግኝቶ የዘመናት እንቆቅልሽ የፈታበት አንዱ ሁነት ነው ያሉት አቶ ላጫ ይህ ደግሞ በብልጽግና ዘመን ብዙ ተስፋዎች እውን የሚሆኑበት እንደሆነ ማሳያ ነው ብለዋል።

በዞኑ በፓርተው እሳቤ የተጀመሩ ስራዎች ይበልጥ በማጠናከር ብልጽግና ለማጽናት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ስርዓትን በመዘርጋት በስንዴ ልማትና በምግብ ራስን ለመቻል በተሰሩ ስራዎች እንዲሁም ውብና ፅዱ አካባቢን በመፍጠር ረገድ የሃገራችን ስም በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ብሎ እየተወሳ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ፓርቲው እነዚህን የልማት ስኬቶች ለማስቀጠል ይተጋል ያሉት አቶ ላጫ አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባትና ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ህዝቡን የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
የተመዘገቡ የልማት ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል እንደ ሀገር የተወጠነውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ በትጋት ይሰራል ብለዋል።
በቀጣይም እንደ ዞንም ሆነ እንደ ሀገር “ኢትዮጲያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል!!

የጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል የዘንድሮ ምርጫ በዞኑ ፍጹም ሰላማዊ፣ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ይሰራል።
ለዚህም አመራሩ ከወትሮ በተለየ መልኩ በትጋት፣ በቁርጠኝነትና በኃላፊነት ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት።

የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ በቃል ብቻ የተገደበ ሳይሆን በተጨባጭ ውጤት የተደገፈ የልማት ውል መሆኑን አቶ አለማየሁ
ተናግረዋል።
በመሆኑም ህዝቡም የፖርቲው እሳቤ እና ርዕይ ተረድቶ ብልጽግና የያዛቸው እቅዶች ተግባራዊ እንዲሆን ከፓርቲው ጎን ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።
በፕሮግራሙ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የብልጽግና ማኒፌስቶ የሆነው የስንዴ ነዶ ርክክብ አድርገዋል ሲል የጉራጌ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ዘግቦታል።

