ጥር 29 /2018(ወልቂጤ)
የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት በ6 ወሩ የተሰሩ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የመንግሥትና የፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የ6ወር የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።
በግምገማ መድረኩ በበጀት ዓመቱ በ6 ወራት የፓርቲ እና በመንግሥት የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች በማስፋት በየዘርፉ የተስተዋሉ ውስንነቶች በማረም ተግባራት ማከናወን እንደሚጠበቅ ተገልጿል ።

አመራሩ የእርስ በእርስ የመተሳሰብና የመደጋገፍ ባህል በማጠናከር እና አደረጃጀቶች በአግባቡ በመጠቀም የህዝባችን የእድገትና የብልፅግና ጉዞ ማረጋገጥ በሚያስችሉ የጋራ ጉዳዮች በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅበት ተመላክቷል።
የአመራር የሀሳብ፣ የአመለካከት፣ አንድነትና ቁርጠኝነት ከፍ በማድረግ ለአንድ አላማ በጋራ በመቆም ተግባርን በውጤት እንዲታይ የተሰሩ ስራዎች ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቁሟል።

አመራሩ አቅሙን በማሳደግና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የፓርቲ ተልእኮ በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል ለህዝብ ጥቅም መስራት ይገባል ።
በግምገማ መድረኩ የወልቂጤ ከተማ ደጋፊና ጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ሀላፊአቶ ሙራድ ያሲን፣ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ፣የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ እና ጠቅላላ የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

